የኢትዮጽያ ታላላቅ ታሪካዊ ቅርሶች | ባህል | DW | 20.06.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የኢትዮጽያ ታላላቅ ታሪካዊ ቅርሶች

የኢትዮጽያን ባህል ሳናወሳ፣ ስለ ኢትዮጽያ ተናገር ማለት አንችልም፣ ምክንያቱም ከሌላዉ አለም ለየት የሚያደርጋት የራስዋ የሆነ ልዩ ባህሏ ነዉና። ስለ ባህሏ ያነሳን እንደ-ሆነ በቅድምያ ስለ ወርቃማ ቡናዋ፣ የቡና ማፍላት ወገዋ ሳንናገር አናልፍም

ሌላዉ ህዝቦችዋ ያላቸዉ የአመጋገብ ባህል የማህበራዊ ኑሮ ወግ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችዋ ሳይጠቀሱ አይታልፉም፣ የኢትዮጽያን ብልጽግና፣ የእድገት ሂደት፣ የህዝቦችዋን ማህበራዊ ኑሮ፣ የስልጣኔዋን እድገት ገላጩን ቅርሷን ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እየጠበቅን ነዉ ወይ? በእንግሊዝ ትራይባል ጋዘሪንግ ሎንደን፣ የተሰኘዉ ድርጅት ከአፍሪቃ ልዩ ልዩ አገሮች ያሰባሰባቸዉን ልዩ ዉበት ያላቸዉ ጥንታዊ ቁሳቁሶች በሚሊዮን በሚቆጠር የኢንግሊዝ ፓዉንድ በመሸጥ ላይ በመሆኑ ነዉ። ይህ ድርጅት የኢትዮጽያ ንብረቶች የሆኑ ዉብ የእንጨት ቅርሳቅርስ ባለቤት መሆኑን በይፋ በድህረ ገጹ በማዉጣት በማጫረት ላይ ይገኛል። የቱሪዝም መስብ የሆነዉ ቅርሳችን በአገራችን የህዝብ ንብረት ሆኖ እንዲቆይ ምን ያህል ቁጥጥር ይደረጋል? ዝርዝሩን አዜብ ታደሰ