የኢትዮጽያ ምሁራኖች በፊደራሊዝምና ዲሞክራሲ ላይ ያደረጉት ዉይይት | ኢትዮጵያ | DW | 25.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጽያ ምሁራኖች በፊደራሊዝምና ዲሞክራሲ ላይ ያደረጉት ዉይይት

በኢትዮጽያ አሁን እየተነገረ ያለዉ ቋንቋንና ብሄር ብሄረሰብን መሰረት ያደረገዉ ፊደራላዊ ስርአት የተሻለ ዲሞክራስያዊ ባህል ሊፈጥር የሚችለዉ የተሻለ የሰብአዊ መብት መከበር እና በመልካም አስተዳደር ሲታጀብ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።

default

ፊደራሊዝምና ዲሞክራሲ በኢትዮጽያ በሚል በሂልተን ሆቴል በቀረበዉ ጥናት ላይ ምሁራኑ የሞቀ ክርክር ማድረጋቸዉ ተገልጾአል። ጥናቱን እና ዉይይቱን በገንዘብ ድጋፍ ያደረገዉ የጀርመኑ Friedrich-Ebert-Stiftung በመባል የሚታወቀዉ ድርጅት ነበር። በቅርቡ በአለም አቀፍ የግጭቶች አስወጋጅ ድርጅት ICGየተሰራ ጥናት እንዳስታወቀዉ በኢትዮጽያ እየተገበረ ያለዉ ጎሳና ቋንቋን መሰረት ያደረገዉ ፊደራላዊ ስርአት ለግጭቶች መባባስ ምክንያት እንደሆነ ማስታወቁ የሚታወስ ነዉ ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ልኮልናል።

ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ