የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግርና ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ | ኢትዮጵያ | DW | 21.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግርና ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደጋጋሚ ለሚካሄደዉ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ የመንግሥት አጸፋ ጠንካራ የኃይል ርምጃ መሆኑን የሀገር ዉስጥም የዉጭ ታዛቢዎችም የሚናገሩት ጉዳይ ሆኗል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:11

ኢትዮጵያ

ለሰብዓዊ መብት የሚቆረቆሩ ተቋማት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደዉ ያልተመጣጠነ የኃይል ርምጃ የጠፋዉ የሰዉ ሕይወ እና የተጎዱት ሰዎች መጠን እና ሁኔታ እንዲጣራ በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ። ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብንም የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት በቸልታ በመመልከት ይተቻሉ። የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሉ የወሰደዉ የኃይል ርምጃ ያስከተለዉ ጉዳት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቋል። አዎንታዊ ምላሽ ባያገኝም። የቀጠለዉ ተቃዉሞ፤ የመንግሥት የኃይል ርምጃ እና የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ የለዘበ አተያይ፤ የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ የዉይይት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic