የኢትዮጵያ ፖለቲካና ፖለቲከኞችዋ፤ ዉይይት | ኢትዮጵያ | DW | 12.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፖለቲካና ፖለቲከኞችዋ፤ ዉይይት

ብዙ ወጣቶች ትምሕርት፤ ደሞዝ፤ ትዳር፤ ፍቅር፤ ከሁሉም በላይ ሕይወታቸዉን የሰዉለት ትግል ለዛሬ እና ለመጪዉ ትዉልድ ያስገኘዉ ዉጤት በጎ መጥፎነት በርግጥ እንደየተመልካቹ የሚለያይ አንዳዴም የሚቃረን ነዉ።ከአርባ እና ከሐምሳ ዓመታት በኋላ አሁንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የዴሞክራሲ፤ የፍትሕ፤ የምጣኔ ሐብት ጥያቄ መልስ አላገኘም የሚሉ ብዙ ናቸዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 36:55

ኢትዮጵያ፤ ያንጋፋና የወጣት ፖለቲከኞችዋ አንድነትና ልዩነት

በተደጋጋሚ እንደተባለዉ የ1960ዎቹ ኢትዮጵያዊ ወጣት የሐገሪቱን መሠረታዊ ፖለቲካዊ፤ ፍትሐዊና ምጣኔ ሐብታዊ ችግሮችን ለማስወገድ ከአደባባይ አመፅ እስከ ሕቡዕ ተቃዉሞ፤ ከፁሁፍ ክርክር እስከ ነፍጥ ፍልሚያ ታግሏል።ከነባሩ ፊዉዳላዊ ሥርዓት ተጠቃሚዎች ጋርም፤ እርስበርስም ተዋግቷን።የደም፤ አካል፤የሕወት መስዋዕትነት ከፍሏል።
ብዙ ወጣቶች ትምሕርት፤ ደሞዝ፤ ትዳር፤ ፍቅር፤ ከሁሉም በላይ ሕይወታቸዉን የሰዉለት ትግል ለዛሬ እና ለመጪዉ ትዉልድ ያስገኘዉ ዉጤት በጎ መጥፎነት በርግጥ እንደየተመልካቹ የሚለያይ አንዳዴም የሚቃረን ነዉ።ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ፤ ከአርባ እና ከሐምሳ ዓመታት በኋላ አሁንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የዴሞክራሲ፤ የፍትሕ፤ የምጣኔ ሐብት ጥያቄ መልስ አላገኘም የሚሉ ብዙ ናቸዉ።ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚታዩ ዉስብስብ ችግሮች በ1960ዎቹ ለትግል የተነሳሳዉን ወጣት የሚወቅሱም አሉ።ለምን? የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ የአንጋፋና የወጣት ፖለቲከኞችዋ አንድነትና ልዩነት በዛሬዉ ዉይይታችን ባጭሩ የምናነሳዉ ጥያቄ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ


 

Audios and videos on the topic