የኢትዮጵያ ፖለቲካና የመገናኛ ብዙኃኑ አጣብቂኝ | ኢትዮጵያ | DW | 11.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፖለቲካና የመገናኛ ብዙኃኑ አጣብቂኝ

ባለፉት አመታት ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው የፖለቲካ ውጥንቅጦች የመገናኛ ብዙኃኑን ሚና ቀይረውታል። በተለይ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልላዊ መንግሥቶች ቁጥጥር ሥር የሚገኙ የራዲዮ እና ቴሌቭዥን ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ተቃውሞች ሲዘግቡ ታይቷል። ለውጡ ግን ለኢትዮጵያ መንግሥት ሹማምንት የሚዋጥ አይመስልም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 26:43

ውይይት፦የኢትዮጵያ ፖለቲካና የመገናኛ ብዙኃኑ አጣብቂኝ

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒሥትሩ በቅርቡ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል፣ ውጥረት ነግሷል" የሚሉ አሉታዊ ዘገባዎች ተበራክተዋል ሲሉ ተደምጠዋል። አዲስ አበባ ላይ በተካሔደ ውይይት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አብዛኞቹን መገናኛ ብዙኃን ወቅሷል። የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ መገናኛ ብዙኃኑ እንዴት ዘገቡት?  የመንግሥት ባለሥልጣናቱስ ትችት ምን ያክል ተገቢ ነው?

እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ 

Audios and videos on the topic