የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ውሎ  | ኢትዮጵያ | DW | 10.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ውሎ 

ከ50 በላይ ሰዎች በሞቱበት የኢሬቻ ተቃውሞ እና አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት ክስ የመሰረተባቸው 9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:42

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ውሎ 

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ዛሬ ሥራ በዝቶባቸው ውሏል። ከ50 በላይ ሰዎች በሞቱበት የኢሬቻ ተቃውሞ እና አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት ክስ የመሰረተባቸው 9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ከሰባት ወራት እስር በኋላ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ግለሰቦች የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ዛሬ ሰጥተዋል። በእነ ቀመር ሐጂ መዝገብ የተካተቱት 9 ሰዎች የሽብር ክስ እንደተመሰረተባቸው ጠበቃቸው ተናግረዋል። የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው ችሎት ብያኔ አልደረሰልኝም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአቶ ዮናታን ተስፋዬ የክስ ሒደት 1 አመት ከ5 ወር አስቆጥሯል። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic