የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ብይንና ተቃዉሞዉ | ኢትዮጵያ | DW | 23.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ብይንና ተቃዉሞዉ

የግንቦት ሰባት ለነፃነት፥ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሐኑ ነጋና የቀድሞዉ የቅንጅት ላንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፀሐፊ አቶ ሙሉነሕ ኢዮኤል በየፊናቸዉ እንዳሉት ፍርዱ ፖለቲካዊ ነዉ

default

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥት ሊያስወግዱና ባለሥልጣናትን ሊግድሉ አሲረዋል ባላቸዉ በተቃዋሚ ፖለቲከኞች፥ በቀድሞ የጦር መኮንኖችና ሌሎች ግለሰቦች ላይ ያሳለፈዉን ብይን የተፈረደባቸዉ ግለሰቦች አጣጥለዉ ነቀፉት።የሞት ቅጣት ከተፈረደባቸዉ አምስት ተከሳሾች መካከል የግንቦት ሰባት ለነፃነት፥ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሐኑ ነጋና የቀድሞዉ የቅንጅት ላንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፀሐፊ አቶ ሙሉነሕ ኢዮኤል በየፊናቸዉ እንዳሉት ፍርዱ ፖለቲካዊ ነዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝሩን ልኮልናል።
የለንደኑ ወኪላችን ድል ነሳ ጌታነሕ ደግሞ እዚያዉ ለንደን የሚኖሩትና ትናንት ሞት የተበየነባቸዉን የግንቦት ሰባት የነፃነት፥ የፍትሕና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌን አነጋግሯቸዉ ነበር።ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌን ጨምሮ አምስቱን ተከሳሾች በሞት ሲቀጣ እድሜ ልክ እስራት ከበየነባቸዉ ሰላሳ-ሰወስት ተከሳሾች መካካል አንዱ አቶ ፅጌ ሐብተ ማርያም የአቶ አንዳርጋቸዉ አባት ናቸዉ።ዝር ዝሩ እነሆ

አበበ ፈለቀ
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic