የኢትዮጵያ ፀረ-አሸባሪነት ሕግና ተቃዉሞዉ | ኢትዮጵያ | DW | 07.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፀረ-አሸባሪነት ሕግና ተቃዉሞዉ

ረቂቅ አዋጁ አሸባሪነትን በመዋጋት ሥም የመንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እንቅስቃሴ ለማገድ ያለመ ነዉ በሚል የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች እንዲሻሻል ሲጠይቁ ነበር

default

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብዙ ሲያወዛግብ የነበረዉን የፀረ-ሽብር ረቂቅ አዋጅ ዛሬ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።ረቂቅ አዋጁ አሸባሪነትን በመዋጋት ሥም የመንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እንቅስቃሴ ለማገድ ያለመ ነዉ በሚል የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች እንዲሻሻል ሲጠይቁ ነበር።ዛሬ የፀደቀዉ አዋጅ ግን ብዙም መሻሻል አልተደረገበትም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ የተቃዋሚ ፓርቲ እንደራሴዎች ደንቡን አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል።

ታደሰ እንግዳዉ/ ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ