የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንትስር መልዕክትና ትርጓሜዉ | ኢትዮጵያ | DW | 08.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንትስር መልዕክትና ትርጓሜዉ

የዉይይታችንን ጥቅል ይዘት «የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መልዕክት፤ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች አፀፋና የሐገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ» ብለነዋል።

ኢሕዴግ ሥልጣን የያዘበትን ሃያ ሰወስትኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በተከታታይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።የበዓሉ ዕለትም ሠፋ ያለ መርሕ ጠቀስ ንግግር አድርገዋል። እስካሁን በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት አምስተኛዉ ብሔራዊ ምርጫ በመጪዉ ዓመት ይደረጋል።የግንቦት ሃያ በዓል የተከበረዉ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት የተደመጠዉም የገዢዉ ፓርቲ የኢሕዴግም፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም ለምርጫ በተዘጋጁበት፤ የፖለቲካ ታዛቢዎች ሥለምርጫዉ ዝግጅት፤ ሥለ የፖለቲካ ማሕበራቱ አቋም በሚተነትኑበት ወቅት ነዉ።በዚሕም ሰበብ የዛሬ ዉይይታችን ጠቅላይ ሚንስትሩ ካስተላለፏቸዉ መልዕክቶች መሐል ሥለ መጪዉ ምርጫና ሥለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናገሩት ላይ ነዉ የሚያተኩረዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic