የኢትዮጵያ ገና በዓል አከባበር | ዓለም | DW | 07.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የኢትዮጵያ ገና በዓል አከባበር

አዲስ አበባ፣ መቀሌ እና ዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ገና በዓል አከባበርን የሚቃኝ መሰናዶ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 17:03

የገና በዓል አከባበር በተለያዩ ከተሞች

የገናን በዓል ዘንድሮ በወጣቶች ዘንድ በምን መልኩ እየተከበረ እንደሆነ ለመቃኘት  የአዲስ አበባው ወኪላችን ወደ ላፍቶ የስፖርት አዳራሽ አቅንቶ ነበር።  በአዳራሹ የገና ዋዜማ የሙዚቃ መሰናዶ አዘጋጆችን እና ታዳሚያንን በቦታው ተገኝቶም አነጋግሯል። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የላከልን ዘገባ በፓትሪያሪክ አቡነ ማትያስ ቃለ-ቡራኬ ይጀምራል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን በማስመልከት በመቀሌ ከተማ  ወጣቶች ከኅብረተሰቡ ገንዘብ በማሰባሰብ ነዳያንን በማብላት እና በማጠጣት በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉት አድርገዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት በመገኘት ወጣቶች ከ200 መቶ በላይ ነዳያንን ሲመግቡ ተመልክቷል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ነዳንያን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አነጋግሯል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለምዶ በዓላትን ብቻ እየጠበቁ የተቸገሩትን መርዳት ላይ ከማተኮር ቋሚ በጀት መድባ እንደምትንቀሳቀስ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የሁለት አብያተክርስትያን አስተዳዳሪዎች ለዶይቸ ቬለ ገልጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችንም ቤተክርስቲያኗ እየረዳች ነው ተብሏል። ቤተ ክርቲያኗ ባላት የእርሻ መሬት ላይ የዶሮ እና የንብ ርባታን በማከናወን የበርማ፣ የኮንጎ እና የሱዳን ዜጎች  ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ  ተገልጿል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

መክብብ ሸዋ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች