የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና ኢትዮጵያውያን በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና ኢትዮጵያውያን በጀርመን

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደነንገጉ እና ለአዋጁም ማስፈፀሚያ ብዙዎች አፋኝ የሚሏቸውን መመሪያዎች ማውጣቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ ከቷል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:21 ደቂቃ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

ርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  በሀገራቸው ጉዳይ ላይ

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዜጎችን በያሉበት እያነጋገረ  ነው ። ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ ዜጎች በአሁኑ ጊዜ ከሚወያዩባቸው እና ከሚጨነቁባቸው ጉዳዮች ውስጥ ሀገራቸው የምትገኝበት ሁኔታ በዋነኛነት ይጠቀሳል ። ርቀው ቢገኙም ዞሮ መግብያቸው በሆነችው በሀገራቸው የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው እና የወገናቸውም ጉዳይ እንደሚቆረቁራቸው በየአጋጣሚው ይገልፃሉ ። እዚህ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ሀገራቸው አሁን ስለ ምትገኝበት ሁኔታ የሚሰማቸውን  እና ለሀገራቸው ሰላም ይበጃል የሚሏቸው መፍትሄዎች አጋርተውናል ። በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ተቀናብሯል ። አዘጋጅዋ ኂሩት መለሰ ታቀርብልናለች  
በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና መፍትሄው  ለዶቼቬለ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደውን ነው የሰማችሁት ።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ከተካሄዱት ተቃውሞች በኋላ መንግሥት የወሰዳቸው ጠንካራ የሚባሉ  እርምጃዎች ዜጎችን ማሳሳበቸው ቀጥሏል ። በተለይ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደነንገጉ እና ለአዋጁም ማስፈፀሚያ ብዙዎች አፋኝ የሚሏቸውን መመሪያዎች ማውጣቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ ከቷል ። ዶቼቬለ በዚሁ

ጉዳይ ላይ ያነጋገራቸው ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያን  ስለ ሀገራቸው በሚሰሙት እና በሚያዩት ማዘናቸውን እና መቆጨታቸውን ነው የተናገሩት ።
በርሊን ነዋሪ የሆኑት እና አቶ በላይነህ ተሾመ የሰጡት አስተያየት ነበር ።ጀርመን ሲኖሩ 28 ዓመት እንደሆናቸው የሚናገሩት የማንሀይም ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አሳየሽ ሮይሽል የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ይከታተሉ ። በመንፈስም ከኢትዮጵያ ተለይተው እንደማያውቁ የሚናገሩት ወይዘሮ አሳየሽ በሚሰሙት እና በሚያዩት ከሀዘንም በላይ ነው የተሰማኝ ይላሉ።በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ይፈፀማል የሚባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ የሚሰጡ ምዕራባውያን መንግሥታት  ግፊት እንዲያደርጉ ደጋግመው ይጠይቃሉ ። ቀደም ካሉት ዓመታት አንስቶ ሲቀርብ የነበረው ይህ ጥያቄ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በቅርቡ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው በፊት ይኽው ጥያቄ ከኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆኑ ጀርመናውያን የመብት ተሟጋቾች ቀርቦላቸው ነበር ። ይህን ጥያቄአቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማቅረብ በርሊን ከተገኙት መካከል የፍራንክፈርቱ ነዋሪ አቶ ደሳለኝ ከበደ ይገኙበታል ።አቶ ደሳለኝ ሜርክል በኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሄደው ያስተላለፉት መልዕክት አቶ ደሳለኝ አርክቷቸዋል ።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውን ሀገራቸው አሁን የገባችበት የፖለቲካ ቀውስ የሚያስጨንቅ እና የሚያሳስብ  ጊዜ ሳይወሰድም መፍትሄ ሊፈለግለት የሚገባ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት ።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች