የኢትዮጵያ የፌደራል ኦዲተር ዘገባ  | ኢትዮጵያ | DW | 30.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የፌደራል ኦዲተር ዘገባ 

ዋና ኦዲተር ገመቹ ደቢሳ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብክነቱ የደረሰው ፣ገንዘብ  በመጉደሉ፣ ባለመወራረዱን እና የወጪ ሰነድ ያልቀረበበትና የፋይናንስ ስርዓት ደንብ በመጣስ ክፍያ በመፈጸሙ መሆኑን አስረድተዋል። በኦዲት ዘገባው በገንዘብ ብክነት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራ አመራር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲዎች ተጠቅሰዋል።

የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ዘገባ በቢሊዮን ብሮች የሚገመት ገንዘብ መባከኑን አስታወቀ። ዋና ኦዲተር ገመቹ ደቢሳ ዛሬ ባቀረቡት ባለ 64 ገጹ ዘገባ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብክነቱ የደረሰው ፣ገንዘብ  በመጉደሉ፣ ባለመወራረዱን እና የወጪ ሰነድ ያልቀረበበትና የፋይናንስ ስርዓት ደንብ በመጣስ ክፍያ በመፈጸሙ መሆኑን አስረድተዋል። በኦዲት ዘገባው በገንዘብ ብክነት ስማቸው በተደጋጋሚ ከተጠቀሰው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራ አመራር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የፌደራል ፖሊስ እና ዩኒቨርስቲዎች ይገኙበታል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝቶ ዘገባውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ 
 

Audios and videos on the topic