የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ  | ኢትዮጵያ | DW | 13.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ 

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል፣ ተቃዉሞዎች ቀጥለዋል። የፌዴራል ስርዓቱን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ክስተቶች እንደሚታዩ መንግሥት ስጋቱን ገልፀዋል።  መንግስት የፖለቲካ ቀዉሱን ለመፍታት ዓመቱን ሙሉ የሚፈፀም እቅድ ማዉጣቱ ታዉቋዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:34

የፀጥታ ሁኔታ

ባለፈዉ ዓርብ የፌዴራልና የዘጠኙም ክልሎች የደህንነት ም/ቤቶች በአገሪቱ የፀጥታና ሰላም ችግር ላይ የጋራ ስብሰባ እንዳደረጉና ችግሩንም ለመፍታት እቅድ እንዳወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርም ደሳለኝ መመራቱ በተነገረዉ በዚህ ስብሰባ ላይ የፌደራል መከላክያ ሚኒስቴር ባለስልጣናት፣የክልሎች ርዕስ መስተዳዳሮች፣ የፀጥታ ሃላፊዎች፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮችና የሚልሻ አዛዦች እንደተሳተፉ ተነግሯል።

አዲስ ስታንዳርድ በድረ ገጹ ባወጣው ለስብሰባዉ ቀረበ በተባለዉ ሰነድ በአገሪቱ ስረዓተ አልበኝነትና እምቢተኝነት ኢየተስፋፋ መሆኑ፣ የሕግ የበላይነት እየተተገበረ እንዳልሆነ እንዲሁም ህዝብ በስጋት ላይ መዉደቁ ተመልክቷል።

የፖለቲካ ቀዉሱን ለመፍታትም የፖለቲካ መፍትሄ መስጠት ተገቢ መሆኑን ሰነዱ ይጠቅሳል። በሰነዱ ህግና ስርዓት እንዲሰፍን የፀጥታ ኃይሎች የሰዎችን ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት እንዲያስከብሩ ፣ ዋና ዋና መንገዶችን እንዲቆጣጠሩ  ፣ ጥፋተኞች ናቸዉ የተባሉትን ለህግ እንዲያቀርቡ፣ ህጋዊ ያልሆኑ ሰልፎችን እንዲቆጣጠሩ እና  ሌሎችም ነጥቦች እንደ ግብ ተቀምጠዋል።

በአገሪቱ ያለዉን የፖለቲካ ችግሮች አገር ዉስጥ ከመፍታት በዉጭ ኃይሎች ላይ ጣት የመቀሰር ሁኔታዎች ይኖራሉ የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ዲግሪያቸው ሰላምና ፀጥታ ላይ ያተኮረ ጥናት የሚያካሂዱት አቶ ዳዊት ዮሴፍ ናቸዉ።

ጉዳዩን አስመልክተን በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ድረ ገፅና በዋትስኣፕ ቁጥራችን ላይ አስተያየታቸዉን የላኩልን አሉ። መንግስት «ሰላማዊ ያልሆነ ተቃዉሞ» መከልከሉ ተገቢ ነዉ ያሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ እስካሁን  ተቃዉሞዎች የሚደረጉት መንግስት ፈቅዶ ሳይሆን የህዝቡ ጭቆና ጣራ ስለደረሰ ነዉ፣ ይህም ጭቆና ካልቆመ ተቃዉሞዉ ይቀጥላል ይላሉ።

ከመንግስት በኩል የበለጠ ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic