የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የርያድ ጉብኝት   | አፍሪቃ | DW | 26.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የርያድ ጉብኝት  

በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሳዑዲ ዓረቢያ ገብቷል። የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያዊያን ተመላሾች እየተስተናገዱበት ያለበትን ሁኔታ የመገምገም ፣ ለሚነሱ ችግሮችም መፍትሄ የመስጠት ዓላማ አለው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:41

በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመራ የልዑካን ቡድን በሳዑዲ


በሌላም በኩል ለረጅም ጊዜ ሲጉላላ የቆየው የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ ኣረቢያ መንግስታት የስራ ውል ስምምነት ትላንት በንግድ ማዕከሏ የጂዳ ከተማ መፈረሙን የኢትዮጵ ኤምባሲ ምንጮች አስታውቀዋል። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ግዛቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የዘጠና ቀን የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ሰላሳ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። በሳዑዲ በህገ ወጥነት ይኖራሉ ተብሎ ከሚገመተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እስካሁን የመውጫ ሰነድ የወሰዱትም ሆነ ወደ ሀገር የተመለሱት ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የጉዞ ሰነድ አሰጣጡን ሂደት ለመገምገምና በኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆነ በሳዑዲ በኩል ተመላሾች ላይ የተፈጠሩ እክሎችን ገምግሞ የማስተካከያ መንገድ በሚፈለግበት  ላይ ለመምከር ሳዑዲ ዓረቢያ ገብተዋል። ትላንት ሐሙስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አዳራሽ የሚከናወኑ የጉዞ ሰነድ አሰጣጥ ሂደቶችን ተመልክተዋል የአንዳንድ ተመላሾችንም ድምጽ ሰምተዋል። ተመላሾቹ በተለይ በሳዑዲ የኢምግሬሽን መስሪያ ቤት ለሚያጋጥማቸው ችግር መፍትሄ እንዲያፈላልጉ በኤምባሲው የተመደቡ ሰራተኞች ስልክ ቁጥሮቻቸው ብዙውን ጊዜ እንደማይነሱ አማረዋል። ሌላው በተመላሾች የተነሳው ችግር የሳዑዲ መንግስት ለዲኤን ኤ ምርመራ ብሎ ያስቀመጠው ጊዜ ለአንዳንዶች ከሚገባው በላይ መራዘሙ ነው። አቶ መለስ ዓለም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደገለጹት የልዑካን ቡድኑ በአጫር ጊዜ ቆይታዉ የተወሰኑ ምልከታዎችን አድርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው በፎቶ ግራፍ አስደግፈው እንዳስቀመጡት ትላንት ማምሻውን ከሳዑዲው አቻቸው ሚስተር አዲል አል ጁቤር ጋር ተወያይተዋል። ዶክተር ወርቅነህ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው በመመለሱ ሂደት የሚፈጠሩ እንቅፋቶችን ለማስወገድ የሳዑዲ መንግስት የበኩሉን ሚና እንዲያጎለብት ጠይቀዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲልም በበኩላቸው ህገወጥ ኢትዮጵያዊያን የእፎይታ እና የምህረት ጊዜው ሳያበቃ በሰላም ወደ ሀገራቸው መግባት እንዳለባቸው አስምረውበታል።የሳዑዲ መንግስትም ህጉን የሚያከብሩ ኢትዮጵያዊን ያለ ምንም እንግልት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ይዘቱ ባይገለጽም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለንጉስ ሰልማን የላኩት ደብዳቤም በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በኩል እንዲደርሳቸው መስጠታቸውን የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ፌስ ቡክ አስፍሯል።
በሌላ ዜን ሲጓተት እና ሲያዘግም የነበረው የኢትዮጵያ እን የሳዑዲ ዓረቢያ የስራ ውል ስምምነት ትላንት በንግድ ማዕከሏ የጂዳ ከተማ መፈረሙን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ እን የቆንስላ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሰል አልይ ገልጸዋል። አቶ ፈይሰል እንዳሉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱልፈታህ አብዱላሂ እና የሳዑዲው አቻቸው ስምምነቱን ፈርመዋል። ይህም  ኢትዮጵያዊያን ተመላሾች በህጋዊ መንገድ ወደ ሳዑዲ ዳግም ሊመጡ የሚችሉበትን መንገድ ያመቻቻል። በሁለቱም ሀገራት እውቅና በሚሰጣቸው ወኪል ተቋማት ወይንም ኤጀንሲዎች አማካኝነት ሰራተኛ የመላኩ ተግባር እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
ይሁንና በኤምባሲው  የፌስ ቡክ ገጽ  የተቀመጠው እና ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩም በራሳቸው ገጽ ያጋሩት ይህ ዜና በተፈራራሚዎቹ ሚንስትሮች ምስል አልተደገፈም። በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን ለተመሳሳይ ጉብኝት ወደ ጂዳ አምርቷል።
ስለሺ ሽብሩ


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ 

ተዛማጅ ዘገባዎች