የኢትዮጵያ የአካባቢዊ ምርጫና ተቃዋሚ ፓርቲዎች | ኢትዮጵያ | DW | 09.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የአካባቢዊ ምርጫና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

የ34 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታ ሳይሻሻል የሚደረግ ምርጫ ከዚሕ ቀደም በሕዝብ ላይ ተፈፀመ ያሉትን እንግልት፥ ስደት፥ እስራትና ሞትን መድገም ነዉ።

default


ኢትዮጵያ ዉስጥ የዲሞክራሲያዊዉ ይዞታ ሳይሰፋና ሳይሻሻል የሐገሪቱ ምርጫ ቦርድ የአካባቢያዊ ምርጫ የሚደረግበትን የጊዜ ሰሌዳ ማዉጣቱን እንደማይቀበሉት የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ። በቅርቡ የተመሠረተዉ የሰላሳ-አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታ ሳይሻሻል የሚደረግ ምርጫ ከዚሕ ቀደም በሕዝብ ላይ ተፈፀመ ያሉትን እንግልት፥ ስደት፥ እስራትና ሞትን መድገም ነዉ። የጊዚያዊ ኮሚቴዉ አባል የሆነዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ ዛሬዉኑ ለብቻዉ በሰጠዉ መግለጫ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ በቅርቡ ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር ተደረገ የሚባለዉ «ፌዝ» ነዉ። መድረክ ከገዢዉ ፓርቲ ጋር ለመደራደር ያቀረበዉ ጥያቄ መልስ ሳያገኝ የምርጫ የጊዜ-ሠሌዳ መዉጣቱንም አጥብቆ ተቃዉሞታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ

DW.COM

Audios and videos on the topic