የኢትዮጵያ የበጀት ፖሊሲና ዕድገት | ኤኮኖሚ | DW | 07.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ የበጀት ፖሊሲና ዕድገት

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባለፈው ሣምንት መንግሥት ለመጪው 2003 ዓ.ም. ያቀረበውን በጀት ተቀብሎ አጽድቋል።

default

ከ 77 ቢሊዮን ብር የሚበልጠው በጀት ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር ሃያ በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን በአገሪቱ ፓርላማ እስካሁን ከጸደቀው ሁሉ ከፍተኛው መሆኑ ነው። ከበጀቱ አብዛኛው በድህነት ቅነሣና በመንገድ ሥራ ላይ እንደሚውል ሲነገር መንግሥት እንደሚለው ይህም በአፍሪቃ ውስጥ ተወዳዳሪ የለውም። በሌላ በኩል የመከላከያና የጸጥታ በጀት ሲጨምር የእርሻ ልማት በጀት በአሥር ከመቶ መወሰኑ ማከራከሩ አልቀረም። ብዙ የሚነገርለት የኤኮኖሚ ዕድገት በሕዝብ የኑሮ ሁኔታ መሻሻል አለመከሰት፣ የዋጋ ግሽበት፣ ሥራ አጥነትና የምግብ ዋስትና ችግር፤ እነዚህ ሁሉ የአገሪቱ ማሕበራዊ ኑሮ ዕለታዊ አጃቢዎች ናቸው። በጉዳዩ የአንድነት ፓርቲ አመራር ዓባል የሆኑትን የኤኮኖሚ ባለሙያ አቶ ተመስገን ዘውዴን አነጋግረናል፤ የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ ክፍል አድምጡ!

መሥፍን መኮንን

ሂሩት መለሰ