የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ | ዓለም | DW | 07.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

በትናንትናዉ ዕለት በጄኔቭ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ይዞታ ሲገመግም አርፍዷል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ቃል የገባችባቸዉን ድንጋጌዎች በተግባር በማዋል በኩል ያሳየቻቸዉን ለዉጦች በዝርዝር ማቅረባቸዉን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ በላከልን ዘገባ አመልክቷል። ገበያዉ በዘገባዉ እንደጠቀሰዉ የተመድ በተለይም የባለድርሻ አካላት ዘገባ በአንፃሩ የኢትዮጵያ መንግስት የተቀበላቸዉን ዓለም ዓቀፍ ድንጋጌዎችንም ሆነ የራሱን ሕገ መንግስት የሚጣረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የፈጸመ መሆኑን አመልክቷል። እንደ አሜሪካ የመሳሰሉ የምክር ቤቱ አባል ሃገራት ተወካዮችም እንዲሁ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች እና ተቃዋሚዎች ላይ የሚፈፅመዉ እስራት፤ እንዲሁም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚመለከተዉ አዋጅና የጸረ ሽብር ሕጉ እንደሚያሳስቧቸዉ አስታዉቀዋል። በመንግስታቱ ድርጅት ሃገራት በየአራት ዓመቱ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸዉ የሚገመገምበት ይህ መድረክ ከጥቂት አመታት በፊት ነዉ የተመሠረተዉ። ኢትዮጵያን በሚመለከት ሲካሄድ የዛሬው ግምገማ ሁለተኛዉ መሆኑ ነዉ።

የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል፤

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic