1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ከሃላፊነታቸው ተሰናበቱ

ዓርብ፣ ሰኔ 28 2016

ኢትዮጵያ ውስጥ በታጣቂ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሚወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት እና የአካል ጉዳት ወይም በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ተባለ። የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ኮሚሽነሩ ከሃላፊነታቸው ይሰናበታሉ ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4hvhD
Äthiopien Addis Ababa | Äthiopische Menschenrechtskommission
ምስል Solomon Muchie/DW

«የጸጥታ ኃይሎች ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ሞት እና ጉዳት ቀጥሏል።» ኢሰመኮ

 


ኢትዮጵያ ውስጥ በታጣቂ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሚወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት እና የአካል ጉዳት ወይም በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ተባለ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያለፈውን አንድ ዓመት የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ዛሬ ይፋ ሲያደርግ ከአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ ጋር በተገናኘ በርካቶች ለተራዘመ እሥር፣ እንግልት፣ ዘለፋ ፣ ድብደባና ሌሎች የመብት ጥሰቶች ተጋልጠዋል ብሏል።

በተያያዘ ኮሚሽኑን ላለፉት አምስት ዓመታት በዋና ኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ በሕግ የተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜ ዛሬ አብቅቷል። ይህንን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ ላይ ሌላ ኮሚሽነር እስከሚሾም ድረስ ተቋሙ በምክትል ዋና ኮሚሽነር እየተመራ ይቆያል ተብሏል። 

ኮሚሽነር ዳንየሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የማበረታታት ጥረት ኤል በቀለ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ከጅምሩ ኃላፊነቱን ሲረከቡ ለአምስት ዓመታት ብቻ ለማገልገል ተስማምተው ነበር ወደ ኃላፊነት የመጡት።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የማበረታታት ጥረት

በሪፖርቱ የተመላከቱ ዋና ዋና የመብት ጥሰቶች 

 

ኢሰመኮ ከሰኔ 2015 እስከ 2016 ዓ.ም ባደረገው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ምርመራ በርካታ ሰዎችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳት ዳርጓል የተባለ የመብት ጥሰት መፈፀሙን፣ በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ መቀጠሉን፣ የመንቀሳቀስ መብት ፈተና ላይ መውደቁን፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፓስት ትእዛዝም ይሁን ከእዙ ትእዛዝ ውጪ የዘፈቀደ እሥር ፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያዎች አስገድዶ መሰወር ከመቀነስ ይልቅ የጨመረ የመብት ጥሰት መሆኑ ተገልጿል።

 

ይህ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል የተባለው የምርመራ ውጤት "የትጥቅ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደቀጠሉ እና እንደተስፋፉ" አመልክቷል።"በትጥቅ ግጭት፣ ግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች እንዲሁም ግጭት በሌለባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ጭምር የሚፈፀሙ ከሕግ ውጪ የሆኑ የሲቪል ሰዎች ግድያ አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል" ሲል ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። የሥልጣን ጊዜያቸው ያበቃው ዶክተር ዳንኤል በቀለ በዚህ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። "አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ ጉዳዮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው በሕይወት የመኖር መብት ነው"።

አሳሳቢዉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የመብት ጥሰት

ሪፖርቱ "ወቅታዊ ሁኔታ" በሚል ምክንያት ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መመዝገባቸውን" አመልክቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ ቢነሳም አሁንም መሰል ጥሰቶች መኖራቸውንም ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገልፀዋል።

"በአስቸኳይ ጉዜ አዋጁ አውድ ውስጥ በርካታ ሰዎች ያለ ኮማንድ ፖስቱ ትእዛዝ ለተራዘመ እሥር ተድልርገዋል"።

ሪፖርቱ "በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ሁኔታ ወይም በሚጣሉ ገደቦች ምክንያት በተለይም በየብስ የሚደረግን እንቅስቃሴ አዳጋች ማድረጉ፤ እንዲሁም የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወይም በታጣቂ ቡድኖች ለተከታታይ ቀናት በሚዘጉ መንገዶች ምክንያት የሚደርሱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች፣ በሸቀጦች ዋጋ እና በገቢ እንዲሁም በጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች ተደራሽነት ላይ የሚደርሱ አሉታዊ ተጽዕኖዎች በዘንድሮ በጀት ዓመትም በተለይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎችም መቀጠላቸው" ተዘርዝሯል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አርማ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "የሰብዓዊ መብት አዋጅ፣ ተቋም እና አሰራርን መፈተሽ ያስፈልጋል፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከሌሎች ሀገራት እና ፍላጎቶች ተጽዕኖ ነፃ መሆን" አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ምስል Solomon Muchie/DW

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "የሰብዓዊ መብት አዋጅ፣ ተቋም እና አሰራርን መፈተሽ ያስፈልጋል፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከሌሎች ሀገራት እና ፍላጎቶች ተጽዕኖ ነፃ መሆን" አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ባለፉት አምስት አመታት በሰብዓነት ላይ የተፈፀመ እና የጦር ወንጀል የሚባሉ ከባባድ እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ያሉት የኃላፉነት ዘመናቸው ያበቃው ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጠንካራ ተቋም ማቋቋማቸውን ተናግረዋል። ተቋሙ "ከማንም ተጽእኖ ደርሶበት እንደማያውቅ" ፣ ቢደርስበትም እንደማይቀበልም ገልፀዋል።

የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለቀጣይ ትኩረት የሚሹ የተባሉት ጉዳዮች

"የትጥቅ ግጭቶች በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ ማድረግ፣ የሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕ ሂደት ተዓማኒ አተገባበር ማረጋገጥ፣ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ወይም የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ማድረግ፤ በሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ሕግ እና ፖሊሲዎች ላይ ማሻሻያ ማድረግ፤ በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች እና የታራሚዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ማሻሻልና ማረጋገጥ፣ የትጥቅ ግጭቶች በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተጽዕኖ፣ እንዲሁም የመንግሥት የፋይናንስና የበጀት እጥረት በተለይም በጤና እና በትምህርት አገልግሎቶች ላይ ያስከተለው ጉዳት ታሳቢ በማድረግ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ዘርፍ የሚከናወነውን ሥራ ማጠናከርና ማጎልበት" የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

ዶክተር ዳንኤል በቀለ
ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን በዋና ኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ በሕግ የተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜ ዛሬ አብቅቷል።ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማሳሰቢያ

የዶክተር ዳንኤል በቀለ የኃላፊነት ጊዜ ማብቃት

ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን በዋና ኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ዶክተር ዳንኤል በቀለ፣ በሕግ የተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜ ዛሬ አብቅቷል። ይህንን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጣዩ ሐምሌ ወር ሌላ ኮሚሽነር እስከሚሾም ድረስ ተቋሙ በምክትል ዋና ኮሚሽነር እየተመራ ይቆያል ተብሏል። 

የተቋሙ የቀድሞው ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ከጅምሩ ይህንን ኃላፊነት ሲረከቡ ለአምስት ዓመታት ብቻ ለማገልገል ተስማምተው እንደነበር እና ያንንም ያደረጉት እንዲህ ያለው ልምምድ ለሀገር ተገቢ እና አስፈላጊ ነው በሚል እንደነበር ገልፀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር