የኢትዮጵያ የረሃብ አደጋና ምክንያቱ | ኢትዮጵያ | DW | 22.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የረሃብ አደጋና ምክንያቱ

በያዝነዉ ምዕተአመት በምስራቅ አፍሪቃ ዉስጥ የተከሰተዉ አስከፊ ድርቅ ከሶማልያ ቀጥሎ በተለይ በሰማንያዎቹ አመታት በከፍተኛ ረሃብ በመመታትዋ የምትታወቀዋን ኢትዮጽያም አዳርሶአል።

default

በአሁኑ ሰአት ስምንት ሚሊዮን ህዝብ ማለት አንድ አስረኛዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ረሃብተኛ ነዉ። አገሪቱ ከተ.መ.ድ የአለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ እርዳታ እንደምታገኘዉ ያህል ሌላ ይህን ያህል እርዳታ የሚወስድ አገር የለም። ባለፈዉ አመት መንግስት በእርሻዉ ዘርፍ የዉጭ ባለሃብትን በማስገባት የእርሻ ለም መሪትን በማከፋፈል ገቢዉን ከፍ ለማድረግ በያዘዉ እቅዱ በርካታ ተቃዉሞን ቀስቅሶበታል። እራሱን የአፍሪቃዉ ነብር ብሎ የሚጠራዉ የኢትዮጽያ መንግስት ከአመታት ጀምሮ ከአስር በመቶ በላይ እድገት እንዳገኘ እና በምርቱ አገሪቷን የዳቦ ቅርጫት እንደሚያደርግ ቢገልጽም በረሃብተኝነት የምትታወቀዉን ኢትዮጽያን ግን ስሟን አላደሰላትም ይላል የዶቸ ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ- አዜብ ታደሰ ታቀርበዋለች።

Äthiopien Landschaft

በሄክታር ለአንድ አመት ሁለት ዶላር- በጋንቤላዉ ለም መሪት እስካሁን 900 የእርሻ መሪት ዉሎች ተፈርመዋል

ሰማሌ መስተዳድር ገና መመለሴ ነዉ። በቀን ምግብ እና የህክምና እርዳታ ለማግኘት አምስት ሰአታት ከሚጓዙ ሴቶች ጋር ተነጋግሪለሁ። አሁንም በርካታ ህጻናት በምግብ እጦት ችግር እየተሰቃዪ ነዉ። አርብቶ አደሮችም የህይወታቸዉ መሰረት የሆኑት ከብቶቻቸዉ እየሞቱባቸዉ ነዉ፥

ባለፈዉ ሳምንት የመንግስታቱ ማህበር የሰብአዊ ጉዳይ ምክትል ዋና ፀሐፊ ቫለሪ አሞስ ምስራቅ ኢትዮጽያን ተዘዋዉረዉ ከጎበኙ በኋላ ለኢትዪጽያ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እንደሚያሰልግ አዲስ አበባ ላይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በጉዳዩ መደንገጣቸዉና ማዘናቸዉ ይታይ ነበር። እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ባለፉት አመታትም ሳይከሰት አልቀረም። ባለፈዉ አመት የኢትዮጽያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአምስት አመት የእድገት እቅድ ሲያወጡ፣ ተስፋ የምናደርገዉ አሉ፣ በእቅዳቸዉ፣ በሚቀጥሉት አምስት አመታት የአገሪቱን ህዝብ ለመመገብ ብቻ ሳይሆን ለዉጭ ሽያጭም የሚሆን የእህል ምርት ለማቅረብ ነዉ። በዚህም እስከ ጎርጎረሳዉያኑ 2015 ድረስ የአገሪቱ የእርሻ ሰብል ምርት በእጥፍ ይጨምራል ነበር ያሉት።
እዚህ ላይ ታድያ ነባራዊዉ እዉነታ ጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀዱት ሳይሆን ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በአገሪቷ ላይ መከሰቱ ነዉ። በያዝነዉ አመት የካቲት ወር ላይ መንግስታቸዉ ከተመድ የአለም ምግብ ፕሮግራም ጋር በጋራ ለሶስት ሚሊዮን ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልፍ ጥሪ አድርገዋል። ይህ ረሃብ ደረሰበት የተባለዉ የህዝብ ብዛት፣ ትክክለኛ አሃዝ ሳይሆን ተቀንሶ መጠቀሱን በረሃብ የተጎዳዉን አኳባቢ ያዩ ምሁራን ይመሰክራሉ። እዚህ ላይ ታድያ ጥያቄዉ የአፍሪቃዉ ነብር ወይስ በእርዳታ ምግብ የሚተዳደር ለማኝ የሚለዉ ነዉ። ከአመታት ጀምሮ ኢትዮጽያ ከአስር በመቶ በላይ እድገት ማሳየትዋ ስትገልጽ፣ በሌላ በኩል ይህ የተጋነነ የእድገት መጠንን አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም በአሃዝ መጠኑን ዝቅ በማድረግ ሲያስተካክል ተስተዉሎአል። ሌላዉ ከአፍሪቃ በህዝብ ብዛት ሁለተኛዋ የሆነችዋ አገር ኢትዪጽያ ከአስር አንዱ ነዋሪዋ የእርዳታ እህል ጥገኛ መሆኑ ነዉ።

Äthiopien Meles Zenawi

ነባራዊዉ እዉነታ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ያቀዱት ሳይሆን


የተመድ በኢትዮጽያ የረሃብ አደጋ የተከሰተዉ ባለፈዉ አመት መጨረሻ የዝናብ መጠን በጣም በመቀነሱ ነዉ ሲል በይፋ ማሳወቁ የሚታወስ ነዉ። በሌላ በኩል በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ ያሉ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በአካባቢዉ በመንግስት ወታደሮች እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አዉጭ ንቅናቄ (ONLF) መካከል ለአመታት በዘለቀዉ ግጭት እና ዉጥረት ምክንያት እርዳታቸዉን መድረስ አልቻሉም። አልፎ አልፎም የአርዳታ ሰጭ ድርጅቶቹ ከቦታዉ እዲወጡ ይደረጋል።

በኬንያ የሚገኘዉ የብሪታንያዉ ግብረሰናይ ድርጅት OXFAM የምስራቅ አፍሪቃ ተጠሪ አሊን ማክዶናልድ እንደሚሉት ረሃቡ በአካባቢ አየር ለዉጥ ብቻ የተከሰተ አይደለም።

« ከረሃቡ ባሻገር ትክክለኛ ያልሆነ እና ሃላፊነት የጎደለዉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሌላዉ አንዱ የችግር ነዉ። ለረሃቡ መባባስ ሰዎች የፈጠሩዋቸዉ በርካታ ችግሮች አሉ። ሌላዉ በረሃብ እጅግ የተጎዱ አካባቢዎች በአብዛኛዉ ስልጣኔ ያልገባባቸዉ በጣም ደሃ እና ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማይታይባቸዉ ቦታዎች ናቸዉ። በዚህ ላይ ደግሞ በአካባቢዉ ላይ ዝናብ ሳይጥል ከቀረ ነዋሪዉ ህዝብ ምንም አይነት የሚተማመንበት ነገር አይኖርም»

በኢትዮጽያ የተጀመረዉ ለዉጭ ባለሃብት የመሪት ይዞታን የየመስጠት ተግባር የዉጭ የእርሻ ድርጅቶች ከህንድ፣ ከቻና፣ ከሳዉዲ አረብያ ጥሩ ለም መሪትን አግኝተዋል። በዚህም መካከል የኢትዮጽያዉ የእርሻ መሪት ይዞታን የሚያከራየዉ ቢሮም የመጀመርያዉን የክራይ ዋጋ እኪሱ አስገብቶ ለወደፊቱ የሚያደርገዉን የኪራይ ሂደት በግልጽ ለማስቀመጥ እቅድ ይዘዋል። እንደዉም የእርሻ መሪት ኪራዪን በተመከተ ኮንትራት እና ዉል መፈጸም ለሚፈልግ በአምደ መረብ በቀጥታ እንዲገኝ ለማድረግ እና ለህዝብ ግልጽ እንደሚያደርግ በይፋ ተነግሮአል። በጋንቤላዉ ለም መሪት ላይ እስካሁን 900 የእርሻ መሪት ዉሎች የተፈረሙ ሲሆን በሄክታር ለአንድ አመት ሁለት ዶላር የተከራየዉ የእርሻ መሪት ላይ ለዉጭ ገበያ አኩሪ አተር፣ ሩዝ ፣ አልያም ነዳጅ ዘይት ለማምረት የሚዉለዉ አትክልት ይበቅልበታል።

Bauer bei der Arbeit in Äthiopien


በኢትዮጽያ ሰማንያ በመቶዉ ህዝብ በግብርና የሚተዳደር ነዉ። አገሪቷ በተደጋጋሚ የሚደርስባትን የረሃብ አደጋ መቋቋም ከፈለገች፣ መንግስት አትኩሮዉን በገበሪዉ ላይ ማድረግ አለበት ይላሉ ብሮት ፎር ዲ ቬልት ዳቦ ለአለም በተሰኘዉ ድርጅት ለረጅም አመታት የአፍሪቃዉ ቢሮ ተጠሪ የነበሩት ጀርመናዊ የምስራቅ አፍሪቃ ጉዳዪች ተመራማሪ ሄልሙት ሄስ

« በጣም በአስቸኳይ መደረግ ያለበት ምርቱን ገበሪዉ በየግሉ እንዲያመርት እና አነስተኛ የእርሻ መሪት ይዞታ ላይ የተሰማሩትን ገበሪዎች በከፍተኛ ደረጃ እገዛ መስጠት ነዉ።»


ሉድገር ሻዶምስኪ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic