የኢትዮጵያ የሥጋ ሽያጭና የስዑዲ አረቢያ እገዳ | ኢትዮጵያ | DW | 26.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሥጋ ሽያጭና የስዑዲ አረቢያ እገዳ

እገዳዉ በመጣሉ ኢትዮጵያ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የዉጪ ምንዛሪ አጥታለች

default

ኢትዮጵያ የዉጪ ምንዛሪ አጥታለች

የስዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያ ዉስጥ የታረዱ ከብቶች ሥጋ ወደ ሐገሩ እንዳይገባ አገደ።ኢትዮጵያ በየወሩ ሰወስት መቶ ሃያ ቶን ትኩስ ሥጋ ወደ ስዕዲ አረቢያ ትልክ ነበር።ይሕን ያሕል መጠን ያለዉ ትኩስ ሥጋ ወደ ስዑዲ አረቢያ የሚልክ ሌላ ሐገር የለም።የስዑዲ አረቢያ መንግሥት ሥጋዉ እንዳይገባ ከሰወስት ሳምንት በፊት በመወሰኑ የኢትዮጵያን ሥጋ ይገዙ የነበሩ ነጋዴዎች ፊታቸዉን ወደ ሕንድና ፓኪስታን አዙረዋል።እገዳዉ በመጣሉ ኢትዮጵያ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የዉጪ ምንዛሪ አጥታለች።የስዑዲ አቢያ መንግሥት እገዳዉን የጣለዉ የኢትዮጵያ የሥጋ ማረጃ ቄራዎች ይዞታ እንዲሻሻል የስዑዲ አረቢያ ሐኪሞች ያቀረቡትን ጥያቄ የኢትዮጵያ ሥጋ አራጆች ገቢር ባለማድረጋቸዉ፥ ወይም መንግሥት ባለማፈፀሙ ነዉ።ነቢዩ ሲራክ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ