የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታ እና የአዉሮጳ ሕብረት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 12.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታ እና የአዉሮጳ ሕብረት

የኢትዮጵያ መንግሥት ለተቃዉሞ አደባባይ በወጡ የኦሮሚያ መስተዳድር ነዋሪዎች ላይ የሚወስደዉን የሐይ እርምጃ የአዉሮጳ ሕብረት እንዲያወግዝ ሒዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ።

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የሕብረቱ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ብራስልስ ዉስጥ ለሚያነጋግሯቸዉ ለኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ለቴዎድሮስ አድሐኖም የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች ሠላማዊ ሠልፈኞችን መግደል፤ ማቁስል ማሰራቸዉን ሕብረቱ እንደሚቃወም በግልፅ መንገር አለባቸዉ።ሒዩማን ራይትስ ዋች እንደሚለዉ የአዉሮጳ ሕብረት «ዝምታዉን ሠብሮ» የኢትዮጵያ መንግሥትን የ«ጭካኔ እርምጃ» ማዉገዝ አለበት።የድርጅቱን የአፍሪቃ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በቀልን በሥልክ አነጋግረነዋል።

ነጋሽ መሃመድ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic