የኢትዮጵያ የምርጫ ቅስቀሳና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሬታ | ኢትዮጵያ | DW | 10.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የምርጫ ቅስቀሳና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሬታ

ፖለቲከኞቹ እንደሚሉት የታገዱባቸዉ ዝግጅቶች በየፓርቲዎቹ አላማዎች የተጠቀሱ ናቸዉ።የኮርፖሬሽኑ ባለሥልጣናት ግን ከሕግ ዉጪ የሠራነዉ የለም ባይ ናቸዉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን (EBC) የተሰኘዉ ማሠራጪያ ድርጅት ለምርጫ ቅስቀሳ የተጠናቀሩ ዝግጅቶችን አላሰራጭ አለን በማለት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወቀሱ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ እና የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎች በየፊናቸዉ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቅድመ ምርመራ እያደረገ ለምርጫ ቅስቀሳ የተጠናቀሩ ዝግጅቶችን አግዷል።ፖለቲከኞቹ እንደሚሉት የታገዱባቸዉ ዝግጅቶች በየፓርቲዎቹ አላማዎች የተጠቀሱ ናቸዉ። የኮርፖሬሽኑ ባለሥልጣናት ግን ከሕግ ዉጪ የሠራነዉ የለም ባይ ናቸዉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ሰወስቱን ወገኖች አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic