የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን እና ዘገባዎቹ | ኢትዮጵያ | DW | 19.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን እና ዘገባዎቹ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በአብዛኛዉ የመንግስት ስላከናወናቸዉ ፍሪያማ ዉጤቶች ላይ ብቻ ዘገባ ያቀርባል ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ነቀፈ።

ባለስልጣኑ ይህን የገለፀዉ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በኢትዮያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች ጋር ባደረገዉ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ተጠሪዎች ጋር ባደረገዉ ዉይይት ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳሪክተር አቶ ልዑል ገብሩ እንደገለፁት የብዙሃን መገናኛዎች የመንግስትን ስኬት ብቻ ይዘግባሉ።በተለይ የሀገራችን የህትመቱን ሚዲያ በሶስት ይከፈላል ያሉት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሪክተር አቶ ልዑል ገብሩ፤ ዘገባዎች ሚዛናዊ ሆነዉ መቅረብ እንዳለባቸዉ ይናገራሉ። መንግስትም ለመተቸት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች