የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ስብሰባ | ኢትዮጵያ | DW | 09.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ስብሰባ

የሁለቱ ምክር ቤቶች ሥስተኛ የስራ ዘመን ከመጀመሩ ከአንድ ቀን አስቀድሞ ለ7 ዓመታት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ያገለገሉት አቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ትኩረት ከሳቡት ጉዳዮች አንዱ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:56 ደቂቃ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ስብሰባ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ የሦስተኛ የሥራ ዘመን አንደኛ የጋራ ስብሰባቸውን ጀመሩ። የሁለቱ ምክር ቤቶች ስብሰባ የተጀመረው በኦሮምያ እና በሶማሌ ክልል ግጭት ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር። የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ያለፈውን ዓመት የመንግሥታቸው አፈጻጸም እና የወደፊቱን የትኩረት አቅጣጫዎች ጠቁመዋል። የሁለቱ ምክር ቤቶች ሥስተኛ የስራ ዘመን ከመጀመሩ ከአንድ ቀን አስቀድሞ ለ7 ዓመታት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ያገለገሉት አቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባት ትኩረት ከሳቡት ጉዳዮች አንዱ ነበር። ስብሰባውን የተከታተተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን አጭር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች