ስብሰባው በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በማስመልከት ሰፊ ውይይት አካሂዷል።የምክር ቤት አባላት ያቀረቧቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ተነጋግሮም የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።ምክርቤቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ አንድ ንዑስ አንቀጽን በጊዜያዊነት አግዷል።
የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የስድሰተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባው በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በማስመልከት ሰፊ ውይይት አካሂዷል።የምክር ቤት አባላት ያቀረቧቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ተነጋግሮም የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።ምክር ቤቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ አንድ ንዑስ አንቀጽን በጊዜያዊነት አግዷል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላትን መሰየምን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን አጽድቆ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መምራቱን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ