የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመቐለ | ኢትዮጵያ | DW | 15.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመቐለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመቐለ ዛሬ ሕዝባዊ ስብሰባ ስያካሂድ ውሏል፡፡ በሕዝባዊ ስብሰባው የኢዜማ ምክትል መሪ አንዷለም አራጌ፣ የሺዋስ አስፋ እንዲሁም ሌሎች የፓርቲው አመራሮች ተገኝተው ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49

(ኢዜማ) በመቐለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመቐለ ዛሬ ሕዝባዊ ስብሰባ ስያካሂድ ውሏል፡፡ በሕዝባዊ ስብሰባው «ውግዘት እና ዘለፋ» አስተናግደናል ያሉት የኢዜማ ምክትል መሪ አንዷለም አራጌ፣ይህም ከመጀመሪያው ዙር የጠበቁት እንደነበር ለ DW ተናግረዋል። ይሁንና የሺዋስ አስፋ እንዲሁም ሌሎች የፓርቲው አመራሮችም ተገኝተው  ፓርቲው ፕሮግራሙን አስተዋውቋል፣ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለቀረቡ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic