የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርና የአይሁድ አዲስ ዓመት | የባህል መድረክ | DW | 17.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የባህል መድረክ

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርና የአይሁድ አዲስ ዓመትኢትዮጵያውያን ቤተ- እስራኤሎች በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት እሑድ መስከረም 2 ቀን 2008 ዓ.ም ማታ አዲሱን የአይሁድ 5776 ዓመት ጀምረዋል፡፡ «ሮሽ ሃሻናህ» በአማርኛ «ርዕስ ዓመት » ኢትዮጵያውያን ቤተ- እስራኤላዉያንን ጨምሮ አይሁዳዉያን «ሮሽ ሃሻናህ» በመባል የሚታወቀውን አዲስ ዓመታቸዉን ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 4 ቀን ማታ ድረስ አክብረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ቀጨኔ አካባቢ በሚኘው ቤተ ሰላም ሲናጉግ «ምኩራብ» የቤተ-እስራኤል ማኅበረሰብ በተገኘበት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ተከብሯል፡፡ በእለቱ ዝግጅታችን ስለአከባበር ሥነ-ስርዓቱ እንዲሁም ስለ አይሁዳዉያን የዘመን አቆጣጠርና ከኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ወይም ባሕረ ሃሳብ ጋር ስላለዉ ተዛማጅነት የሚነግሩንን ባለሞያዎች ይዘናል።

Audios and videos on the topic