የኢትዮጵያ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች ፈተናና እድሎቻቸዉ | ኢትዮጵያ | DW | 05.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች ፈተናና እድሎቻቸዉ

በዕለቱ የእንወያይ ቅንብር የኢትዮጵያ ወጣት የስራ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸው ፈተናዎችና ዕድሎቻቸው በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ከሦስት ባለሙያዎች ጋር ውይይት አዘጋጅተናል። በውይይቱ የቆዳ ውጤቶችና የልብስ ዲዛይነር ዮናታን በቀለ፤የሶፍትዌርና ድረ-ገጽ ባለሙያ ሳሙኤል አርከበ እና የኢኮኖሚ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ ተሳትፈዋል።

የዉይይቱ ተሳታፊ ወጣት ዮናታን በቀለ የቆዳ ውጤቶችና የልብስ ዲዛይነር እንደሚሉት፤''ስጀምር ቦርሳዎችን በመስራት ነበር መጀመሪያ የተማርኩት። ድርጅቶች ውስጥ ከገባሁ በኋላ የቆዳ ልብሶችንም አንድ ላይ ጎን ለጎን ማስኬድ ጀምሬ ነበረ።

ከዛም ክህሎቴን ለማሳደግ ስል በፋሽን ዲዛይን ተምሬ የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን ከቆዳ ጋር በማድረግም ሊሆን ይችላል እየሰራሁ ነበር። ራስን ለመቀየር ሁልጊዜ የራስህን ስትሰራ ነው ውጤታማ ልትሆን የምትችለውና በዛ ላይ ተመርኩዤ የራሴ የሆነ ትናንሽ ነገሮች ለመስራት አስቤ ነበር። አንድ ማሽን ለጊዜው ገዛሁኝ።ማሽን ከገዛሁ በኋላ ግን መስሪያ ቦታ ችግር ነበር። ማሽኑን ዘመድ ጋር አድርጌ ነበር የምሰራው። በትልቅ ደረጃ ለመንቀሳቀስ ብዙ ነገሮች ያግዱሃል። በገንዘብ ደረጃ ብዙ ዝግጁ አልነበርኩም። በዛ የሚደግፍ ሰው አልነበረም። ቦታም የማግኘት እድል የለም። ብር ኖሮህ እንኳን ቦታ ለማግኘት ተከራይተህ ነው። እኛ ሃገር ደግሞ ተከራይተህ ለመስራት የቤት ኪራይም ውድ ነው የሚሆንብህ። በዚህ መንገድ መስራት አስቸጋሪ ስለነበር ቤት ውስጥ ለመስራት ተገድጄ ነበር። አንዳንድ ስራዎችን እሰራ ነበር። ነገር ግን ያስ ስራ አልተሳካም። ከዛ በኋላ ስራውን ለመቀጠል ብዙ ስራዎች አጋጥመውኛል። '' ወጣት ዮናታን በቀለ የቆዳ ውጤቶችና የልብስ ዲዛይነር

''አብዛኞቹ ለምሳሌ ምንድነው የሚሉት አይ ትንሽ ሰብሰብ አድራችሁ ብር ተቀብላችሁ ትሄዳላችሁ ነው የሚሉት። የእምነት የመተማመን ችግር ነበር። መሰረተ ልማቱ ጥሩ የኢንተርኔት አገልግሎት ያለበት ጊዜ አልነበረም። የመጀመሪያ አገልግሎታችንን ስንጀምር እኛው ራሳችን ከአንድ ቢሮ እስከ ሌላኛው ቢሮ እየሄድን እያንኳኳን እየገባን አገልግሎቱን እያሳያን ሰዎች እስኪለምዱት ድረስ የሙከራ ጊዜ እየሰጠን ነበር''

ወጣት ሳሙኤል አርከበ የሶፍትዌርና ድረ-ገጽ ባለሙያ ፤''እነዚህ ኩባንያዎች ሳሙኤል፤ዮናታን እና ብዙ ልጆች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጀምሯቸው ኩባንያዎች ጥሩ የቢዝነስ ሃሳብ ይዘው መጥተው መሃል ላይ የሚቀሩት አንዱ ምክንያት የገንዘብ ችግር ነው። ሁለተኛው ደግሞ የመሰረተ ልማት ችግር ነው። የስልክ፤የኢንተርኔት አገልግሎቶች መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው። የትኛውም ቢዝነስ እንዲያድግ የመብራት የውሃ ግልጋሎቶች መኖር አለባቸው። ሶስተኛው በክህሎት ደረጃ አለን ወይ? ነው። ተማሪዎች በኮምፒውተር ሳይንስ በኢንጂነሪንግ እየተማሩ ይወጣሉ ግን የእኛ የትምህርት ስርዓት አዲስ ግኝትንና ፈጠራን (innovation & creativity) የሚያስተምር ነወይ?እነዚህን ነገሮች ማምጣት አለብን። በስልጠና እነዚህ ነገሮች እስካልመጡ ድረስ አሁንም ቢሆን እነዚህ አዳዲስ ስራዎች ችግር ያጋጥማቸዋል።'' ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic