የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣት እና የተመድ | ኢትዮጵያ | DW | 03.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የተመድ አስተያየት ስለ ኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣት

የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣት እና የተመድ

በተመድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ሆዜ ሉስየስ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ከሶማልያ ወታደሮችዋን እንደምታስወጣ አስቀድሞ አልተነገረውም ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:28 ደቂቃ

የተመድ አስተያየት

ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ ስታስወጣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳላሳወቀች ተነገረ ። በተመድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ሆዜ ሉስየስ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ከሶማልያ ወታደሮችዋን እንደምታስወጣ አስቀድሞ አልተነገረውም ። የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያ  በራስዋ ወጭ ሶማሊያ ያዘመተቻቸውን ወታደሮቿን በገንዘብ ችግር ምክንያት እንዳስወጣች ባለፈው ሳምንት ተናግረው ነበር ። የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን ሉስየስ እንዳሉት ድርጅታቸው  የኢትዮጵያ ወታደሮች በመውጣታቸው የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ሌሎች አባላትን እየጠየቀ መሆኑን አስታውቀዋል ።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic