የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካ-ከዶክተር ነጋሶ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ | ኢትዮጵያ | DW | 07.12.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካ-ከዶክተር ነጋሶ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ከሌሎቹ የፖለቲካ ማሕበራትን አንድነትን-ከመረጡበት ብዙ ምክንያቶች የፓርቲዉ መሪ ጥንካሬና ሴትነት- አንዱ ነዉ።በወይዘሪት ብርቱካን-ምክንያት።

default

07 12 09


የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳና የቀድሞዉ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ስዬ አብረሐ ለምሥረታዊ አበክረዉ የጣሩለት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዲሞክራሲያዊ መድረክ ወደ ጥምረት-ሲያመራ፥ ሁለቱ ፖለቲከኞች የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ተቀይጠዋል።ሰሞኑን።ዶክተር ነጋሶን ዛሬ-ለምን እና እንዴት ብለናቸዋል።ከመድረክ ምሥረታ ሒደት ይጀምራሉ።እንስማቸዉ።
ድምፅ

የምርጫዉ ሒደት በምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ድርድር ነዉ-የተጀመረዉ። የምርጫዉ ሥነ-ምግባር ይዘት በተለይም የድርድሩ ሒደት ትልቁን ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበራት ስብስ- መድረክን ቅር ቢያሰኝም-ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ እና ሰወስት ተቃዋሚዎቹ የተስማሙበትን ሐሳብ-ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መቀበላቸዉ ተሰምቷል።ዶክተር ነጋሶ ግን ደንቡን-ለዲሞክራሲ አደገኛ ይሉታል።
ድምፅ
ግን ለምን።
ድምፅ
ያም ሆኖ ደንቡ ሕግ እንዲሆን ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።
ድምፅ
ዶክተር ነጋሶ-አደገኛ ያሉት አዋጅ-ሕግ ከሆነ የተቃዋሚዎች በተለይም የመድረክ ሚና-ምንነት በርግጥ ያነጋግራል።መልስ አላቸዉ።ዶክተር ነጋሶ-ከፕሬዝዳትነት ሥልጣናቸዉ ሲሰናበቱ-በፕሬዝዳትነት ያገለገለ-ፖለቲከኛ የፖለቲካ ፓርቲ አባል እንዳይሆን በሕግ-ተደንግጓል።ሕጉ አልተሻረም።እሳቸዉ ግን-የአንድነት ፓርቲን ተቀላቅለዋል።
ድምፅ
ይላሉ።ሌላም-ምክንያት አላቸዉ።ከሌሎቹ የፖለቲካ ማሕበራትን አንድነትን-ከመረጡበት ብዙ ምክንያቶች የፓርቲዉ መሪ ጥንካሬና ሴትነት- አንዱ ነዉ።በወይዘሪት ብርቱካን-ምክንያት።
ድምፅ
እነዚሕንና ሌሎችንም-አንስተናል።ሳምንት ጠብቁን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ እስከዚያዉ ቸር ያሰማን።

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic