1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና የ «ኦዴፓ» አቋም

ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2011

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ «ODP» ሕገ-መንግሥቱ እየተናደ ነው ፡ ፌዴራሊዝሙ ፈርሷል ፡ አሃዳዊ ስርአት ለመመስረት እየተሠራነው የሚሉ እና ሌሎች የሃሰት ፕሮፖጋንዳዎች በመገናኛ ብዙኃን ፡ ምሁራን እና ማህበራዊ መገናኛዎች መከፈታቸውንና ይህንንም እንደማይቀበለው ለ«DW»ተናገረ፡፡

https://p.dw.com/p/3Dg3G
Taye Dendea
ምስል Geberu Godane


የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ «ODP» ሕገ-መንግሥቱ እየተናደ ነው ፡ ፌዴራሊዝሙ ፈርሷል ፡ አሃዳዊ ስርአት ለመመስረት እየተሠራነው የሚሉ እና ሌሎች የሃሰት ፕሮፖጋንዳዎች በመገናኛ ብዙኃን ፡ ምሁራን እና ማህበራዊ መገናኛዎች መከፈታቸውንና ይህንንም እንደማይቀበለው ለ«DW»ተናገረ፡፡ ሕገ- መንግሥቱ እስካልተስተካከለ እና በሥራ ላይ እስከሆነ ድርስ መከበር አለበት ፡ ፌዴራሊዝም ለሀገሪቱ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ላይ ድርድር እንደሌለውም የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት የህዝብ አስተያየት እና ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታየ ደንደአ ለDW ተናግረዋል፡፡ ፓርቲው የኦሮሞ ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄዎች ናቸው ያላቸውን የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳዮች ለመመለስ እንደሚሠራም ኃላፊው የተናገሩ ሲሆን አፋን ኦሮሞ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን የሚለው የፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን የሌሎች ፓርቲዎችና  የህዝቡ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄው እንዲመለስ እንሠራለን ብለዋል፡፡  በአዲስ አበባ ጉዳይም ሌሎችን የከተማዋን ነዋሪዎች ጥቅም በማይጎዳ መልኩ የሚነሱ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችን እንመለከታቸዋለን ብለዋል፡፡


ሰለሞን ሙጬ


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ