የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መቀጣት፤ | ስፖርት | DW | 23.01.2013
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መቀጣት፤

የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን፤ (CAF)ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ከእንግዲህ እስከ ውድድሩ ፍጻሜ የጋጠ ወጥነት ተግባር ካልፈጸሙ 5ሺ አለበለዚያ 10 ሺ ዶላር ቅጣት

በፌደሬሽኑ ላይ የሚጣልበት መሆኑን አስታውቋል። ከ 31 ዓመታት ወዲህ ፤ ወደ አፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የተመለሰችው ኢትዮጵያ፣ ባለፈው ሰኞ ከዛምቢያ ጋር ባደረገችው ግጥሚያ ተመልካቾችን ያረካ፤ የእግር ኳስ ሐያስያንንም ያስደነቀ እንቅሥቃሴ በማሳየት 1-1 መለያየቷ

የሚታወስ ነው። ስለተጣለው ቅጣትና ቀጣዩ ጨዋታ ፣ የፌደሬሽኑን አባልና የእስፖርት ጋዜጠኛ አቶ መላኩ አየለን በማነጋገገር በማነጋገር ተከታዩ ዘገባ ተጠናቅሯል።ኢትዮጵያ ከትናንት በስቲያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኔልስፕሪዩት በተባለችው ከተማ፣ በእምቦምቤላ ስታዲዬም፣ ከዛምቢያ ጋር ባደረገችው ግጥሚያ ፣ በዚያ ተገኝተው ለቡድኑ ሞቅ ያለ የሞራል ድጋፍ የሰጡት ኢትዮጵያውያን፣ እንዲያ

ማበረታታቸው ቢያሥመሰግናቸውም፤ አንዳንዶች በፈጸሙት ህገ-ወጥ ድርጊት ፌደሬሽኑ ቅጣት ተጥሎበታል። የቅጣቱ ሰበብ በእርግጥ ምንድን ነው? የፌደሬሽኑ አባልና የእስፖርት ጋዜጠኛ አቶ መላኩ አየለ---በዚያው በእምቦቤላ ስታዲዬም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሞቅ ያለ ድጋፍ የሰጡ ብቻ ሳይሆን «አሉ»ያሏቸውን «የሰብአዊ መብት ጥሰቶች» በ T-SHIRT አማካኝነት ያንጸባረቁ እንደነበሩ የጠቆሙ መረጃዎችም አሉ።የተጣለውን ቅጣት በተመለከተ ፣ አንድ የአግር ኳስ ፌደሬሽን ይመለከተኛል ብሎ ለመቀበልም ላለመቀበል፣ ደጋፊዎች የሚባሉትን እርሱም ሆነ CAF በምን መለኪያ ነው የሚያውቋቸው!?በተጠቀሰው ስታዲዬም በመገኘት ጨዋታውን ከተመለከቱት ደጋፊዎች መካከል በአዲስ አበባና በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ሁለት ኳስ አፍቃሪዎች እንዲህ ብለዋል---።

ስለቀጣዩ ግጥሚያ ዝግጅት---አቶ መላኩ አየለ---።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 23.01.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17QT6
 • ቀን 23.01.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17QT6