የኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግርና መፍትሄው | ስፖርት | DW | 19.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግርና መፍትሄው

በአፍሪቃ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር ቢቀር በአፍሪቃ አንዴ ገናና የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት ውድቀትም በአገሪቱ ተወላጆች ዘንድ መልሶ መነጋገሪያ ጉዳይ እንዲሆን አድርጓል።

default

ለመሆኑ ውድቀቱን ምን አመጣው? መፍትሄ የሚገኘውስ እንዴት ነው? በበኩላችን ትናንት በዕሑድ መድረክ ፕሮግራማችን በጉዳዩ ሰፊ ውይይት ስናካሂድ ዛሬ ደግሞ ከአገርቤት የተለያዩ አስተያየቶችን አጠናቅረናል። ታዲያ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት ውድቀት ማነጋገር የያዘው ባለሥልጣናትና የስፖርቱን ባለሙያዎች ብቻ አይደለም። ብዙዎች ዜጎችም እንዲሁ በጉዳዩ ሃሣባቸውን እየገለጹ ነው።

በወጣቶች ተሃንጾ ላይ በሰፊው ከማተኮሩ አስፈላጊነት ባሻገር የአገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሺን ነጻነቱን መጠበቁና ተግባሩን ቀና ማድረጉ፤ ሙስናና የዝምድና አሠራር መወገዱ፤ ቀጣይነት ያለው አሠራር መስፈኑ ወዘተ. በመፍትሄነት ከያቅጣጫው ይጠቀሳሉ።

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድቀት መፍትሄ ለማፈላለግ በሚደረገው ጥረት የትናንቱም ሆነ የዛሬው ውይይት ለፌደሬሺን ባለሥልጣናት፣ ለስፖርቱ ጠቢባንና ለዜጎች በሙሉ የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው አይሆንም። እና ወደፊትም የመፍትሄ ሃሣባችሁን ብታካፍሉን ትኩረት ሰጥተን እናስተናግዳለን።

መሥፍን መኮንን

ተክሌ የኋላ