የኢትዮጵያ እግር ኳስ በዓለም መድረክ | ስፖርት | DW | 04.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ በዓለም መድረክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ዘላቂ ውጤት ያጣበት ምክንያቱ ምንድን ነው?ብሔራዊ ቡድኑ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ዘላቂ ውጤት ከራቀው ቆይቷል። በእርግጥ ቡድኑ እጎአ በ1962 ዓም የአፍሪቃ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን የበቃ ነበር።

በምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ ጨዋታዎችም ዋንጫ ለማግኘት ችሏል። ሆኖም ጠንካራ በሚባሉ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የአፍሪቃ ዋንጫን ጨምሮ በዓለም አቀፍ መድረኮች ዘላቂ ውጤት ማግኘት ተስኖታል። የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያን እንኳን ማለፍ የቻለው ባለፈው የአፍሪቃ ዋንጫ ከ31 ዓመታት በኋላ ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ዘላቂ ውጤት ያጣበት ምክንያቱ ምንድን ነው?

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic