የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰላም ስምምነት አተገባበር እና ሂደቱ | ኢትዮጵያ | DW | 20.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰላም ስምምነት አተገባበር እና ሂደቱ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶክተር ማርቆስ ተክሌ «ስምምነቱ ተግባራዊ ያልሆነው ኤርትራ የአልጀርሱ ስምምነት በቅድሚያ እንዲተገበር እና አወዛጋቢው ድንበር በግልጽ እንዲለይ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጧ ነው» ተብሎ የሚነገረው አስተያየት አግባብነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:28

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ስምምነት አተገባበር እና ሂደቱ

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለፈው ዓመት የተደረሰው የሰላም ስምምነት የአፈጻጸም ችግር ገጥሞታል በሚል በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን የሚሰራጨው አስተያየት ከዕውነት የራቀ መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን አስታወቁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶክተር ማርቆስ ተክሌ ሥምምነቶቹ ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖራቸውና ተቋማዊ እንዲሆኑ በማድረግ ሂደት አፈጻጸሙ መዘግየቱን በተለይ ለዶይቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። «ስምምነቱ ተግባራዊ ያልሆነው ኤርትራ የአልጀርሱ ስምምነት በቅድሚያ እንዲተገበር እና አወዛጋቢው ድንበር በግልጽ እንዲለይ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጧ ነው» ተብሎ የሚነገረው አስተያየት አግባብነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል። ከዚሁ ጋር መንግሥት ከኤርትራም ሆነ ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ከሕዝብ የተደበቀ እና የአገሪቱንም ጥቅም የሚጎዱ አንዳችም ስምምነት አለማደረጉንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው ያብራሩት። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ 

Audios and videos on the topic