የኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የዓለም ባንክ | ኢትዮጵያ | DW | 20.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የዓለም ባንክ

ባንኩ እስካሁን የሚያደርገዉን ድጋፍ በሚቀጥሉት ሰወስት ዓመታትም መስጠቱን ይቀጥላል።የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን አድጓል የሚባለዉ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት የሕዝቡን ኑሮ ይበልጥ ከማክበድ ሌላ የጠቀመዉ ነገር የለም ባዮች ናቸዉ።

Der Meskal Square im Zentrum der äthipischen Hauptstadt Addis Abeba von der großen Tribüne aus gesehen, links im Bild die kürzlich installierte Video-Wand. Aufnahme vom Januar 2007. Foto: Peter Smolka +++(c) dpa - Report+++

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ መንግሥት ለነደፈዉ የአምስት ዓመት የዕድገትና የለዉጥ ዕቅድ ድጋፍ መስጠቱን እንደሚቀጥል አስታወቀ።የባንኩና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ባደረጉት ዉይይት ላይ እንደተገለጠዉ ዓለም አቀፉ አበዳሪ ተቋም «ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት አሳያች» ባለዉ የምጣኔ ሐብት ዕድገት ረክቷል።ባንኩ እስካሁን የሚያደርገዉን ድጋፍ በሚቀጥሉት ሰወስት ዓመታትም መስጠቱን ይቀጥላል።የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን አድጓል የሚባለዉ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት የሕዝቡን ኑሮ ይበልጥ ከማክበድ ሌላ የጠቀመዉ ነገር የለም ባዮች ናቸዉ።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic