የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምግብ ዝግጅት ተቋም | ኢትዮጵያ | DW | 31.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምግብ ዝግጅት ተቋም

የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ለደንበኞቹ የሚያቀርበውን ምግብ የሚያዘጋጅበት ተቋም ሥራ አስጀመረ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:37
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:37 ደቂቃ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

በ11,500 ስኩዌትር ሜትር ላይ ያረፈው ባለ አንድ ፎቅ የምግብ ማብሰያ እና የመጋገሪያ ማዕል በዘመናዊ የኩሽና እቃዎች፤ የማጠቢያ ማሽኖች፤ ማቀዝቀዣዎች የተሟላ እንደሆነ ተነግሮለታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ መድሕን እንደገለጡት አዲሱ ለአየር መንገዱ ደንበኞች ምግብ የሚዘጋጅበት ይኸው ተቋም ከአፍሪቃ ግዙፉ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰባተኛ የንግድ ቅርንጫፍ የሆነው የምግብ ማዘጋጃ ማዕከል እንጀራን ጨምሮ የቻይና፤ ሕንድ፤ ኦቶማን፤ የጣልያን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የምግብ አይነቶችን ለደንበኞቹ ያቀርባል ተብሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው የምግብ ዝግጅት የደሕንነት ቁጥጥር ሕግጋት ይመራል የተባለለትን እና 100,000 ምግቦችን አዘጋጅቶ የማቅረብ አቅም ያለውን ተቋም የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ጎብኝቶ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic