የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወረቀትን ከአሰራሩ አሰናበተ | ኢትዮጵያ | DW | 02.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወረቀትን ከአሰራሩ አሰናበተ

የአየር መንገዱ ዋ/ሥራ አስፈጻሚ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻውን የወረቀት ሰነድ ፈርመው ያገለገሉ ወረቀቶችን በማቃጠል ወደ ኤሌክትሮኒክ የተቀየረውን የአሰራር ሽግግር ይፋ አድርገዋል። ዋ/ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገ/ማርያም አየር መንገዳቸው ላለፉት 10 አመታት ወረቀትን ከግልጋሎት ውጪ ለማድረግ መጣሩን በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:28 ደቂቃ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ አደረገ

 

ከአሁን በኋላ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና፤ የበረራ፤ የንግድ የፋይናንስ፤ የሰው ሐይል አስተዳደር፤ የደንበኞች አገልግሎት የግዢ አቅርቦት ሥራዎች በሙሉ በኤሌክትሮኒክ የሚከወኑ ይሆናል። አቶ ተወልደ እንደተናገሩት ባለፉት አምስት አመታት ኩባንያቸው የአሰራር ሽግግር ለማድረግ በኢንፎርሜሽን ኮምዩንኬሽን ቴክኖሎጂው ዘርፍ የ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን ገልጠዋል። ሽግግሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በወጪ ቁጠባ እና የአሰራር ቅልጥፍናን በማሳደግ  ውጤታማ ያደርገዋል ተብሏል። ካሁን በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የጉዞ ቲኬቶቻቸውን በድረ-ገፅ መቁረጥ ይችላሉ።

አየር መንገዱ ደንበኞቹ በተንቀሳቃሽ ስልክ በሚቀርበው የባንክ አገልግሎት አማካኝነት ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ዳሸን ባንክ እና ኅብረት ባንክ ጋር ሥምምነት ፈፅሟል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic