የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋና ምርመራዉ | ኢትዮጵያ | DW | 17.01.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋና ምርመራዉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሐላፊዎች ግን የሊባኖስ ባለሥልጣናትን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ አድርገዉታል።ሐላፊዎቹ እንደሚሉት አደጋዉ የደረሰዉ አዉሮፕላኑ አንድም በሚያሳዬል አለያም በመብረቅ በመመታቱ ነዉ።በአደጋዉ አዉሮፕላኑ ያሳፈራቸዉ ዘጠና ሰዎች በሙሉ አልቀዋል

default


የኢትዮጵያ አየር መንገድ፥ ዛሬ ሁለት ዓመት ግድም ሊባኖስ ርዕሠ-ከተማ ቤይሩት አጠገብ ከነመንገደኞቹ ሥለጋየዉ አዉሮፕላኑ የሊባኖንስ ባለሥልጣናት ይፋ ያደረጉትን የምርመራ ዉጤት እንደማይቀበለዉ አስታወቀ።የሊባኖስ ባለሥልጣናት አደጋዉ የደረሰዉ በአዉሮፕላኑ አብራሪና በረዳታቸዉ ሥሕተት ነዉ ባዮች ናቸዉ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሐላፊዎች ግን የሊባኖስ ባለሥልጣናትን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ አድርገዉታል።ሐላፊዎቹ እንደሚሉት አደጋዉ የደረሰዉ አዉሮፕላኑ አንድም በሚያሳዬል አለያም በመብረቅ በመመታቱ ነዉ።በአደጋዉ አዉሮፕላኑ ያሳፈራቸዉ ዘጠና ሰዎች በሙሉ አልቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic