የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራና እቅድ | ኤኮኖሚ | DW | 30.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራና እቅድ

አየር መንገዱ ወደ ፍራንክፈርት ጀርመን በረራ የጀመረበትን 55 ተኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ፍራንክፈርት ውስጥ ባሰበበት ወቅት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም እንደተናገሩት ድርጅታቸው 2025 በተሰኘው እቅዱ በርካታ ውጥኖቹን ተግባራዊ አድርጓል ።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሰባት ዓመታት የላቀ እድገት ለማስመዝገብ መብቃቱን የአየር መንገዱ ሃላፊ አስታወቁ ። አየር መንገዱ ወደ ፍራንክፈርት ጀርመን በረራ የጀመረበትን 55 ተኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ፍራንክፈርት ውስጥ ባሰበበት ወቅት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ድርጅታቸው 2025 በተሰኘው እቅዱ በርካታ ውጥኖቹን ተግባራዊ አድርጓል፤ የተቀሩትንም ከግብ ለማድረስ እየጣረ ነው ። በካርጎ አገልግሎት መዘግየትና መንገደኞችን በማስተጓጓል አየር መንገዱ ስለ ሚቀርብበት ወቀሳ ዶቼቬለ የጠየቃቸው የፍራንክፈርት የስራ ሃላፊ ችግሮቹን ለማስወገድ የመፍትሄ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል ። በፍራንክፈርቱ ስነስርዓት ላይ የተገኘው የወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝሩን ያቀርብልናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic