የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ተሸለመ | ስፖርት | DW | 21.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ተሸለመ

ኢትዮጵያ በለንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፈው ብሔራዊ ቡድን ሽልማት አበረከተች።በውድድሩ ወርቅ ላሸነፉ ሁለት አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ብር ፤ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ ደግሞ 30 ሺህ ብር ተሸልሟል። አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ እና አሰልጣኝ ሶሪሳ ፊዳ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 08:58
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
08:58 ደቂቃ

ስፖርት፣ ነሀሴ 17፣ 2009 ዓም

በ16ኛዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን  በመወከል ለንደን ከትሞ የነበረው የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን 2 የወርቅ እና 3 የብር ሚዳልያ በአጠቃላይ  5 ሚዳልያ  በመያዝ  በውድድሩ ከተሳተፉት ሀገራት 7ኛ በመሆን ወደ ሀገሩ ከተመለሰ ሁለተኛ ሳምንቱን ይዟልከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በአራራት ሆቲል በተደረገ የሽልማት ዝግጅት  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዮሚፍ ቀጀልቻን አና ከአልማዝ አያን ጀርባ ያለውን ባለቤትዋን አሰልጣኝ ሶሪሳ ፊዳን  የለንደን አለም ሻምፒዮና ልዩ ተሸላሚ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ ለነኝህ ልዪ ተሽላሚዋች ወርቅ ሚዳልያ ካመጡት አትሊቶች መሳ ለማሳ  40 ሺህ ብር ሽልማት ሲያበረክት  ማበርም ማማርም መክበርም በህብረት ማሆኑን ላሳየው አትሌት ዪሚፍ ቀጀልቻ  የቡድን መሪው ገብረእግዚአብሄር ገብረማሪያም የራሱን ተጨማሪ 40 ሺህ ብር ሽልማት አበርክቶለታል። ወርቅ ያመጡት አልማዝ አያና እና ሙክታር እድሪስ እያንዳንዳቸው 40 ሺህ ብር ሽልማት ሲያገኙ  የብር ሜዳሊያ ያመጡት ጥሩነሽ እና ታምራት 30 30 ሺህ ብር ተሸልመዋል።ሽልማቱ ምን  አልባት ብዙ ላይሆን ይችላል ነገር ግን የ ግለሰቦችን  ልባዊ ጥረት አና ሀገር ፍቅር  ዋጋ ለመስጠት አንዲሁም ተተኪውን ትውልድ ለማበረታታ የተደረገ ነው ሲሉ  የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን የሀብት  አሰባሰብ እና የግንኙነት ሀላፊ ምንትዋብ ግደይ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ሐና ደምሴ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic