የኢትዮጵያ አቋም፣ ተመድና የትግራይ ግጭት | ኢትዮጵያ | DW | 09.07.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አቋም፣ ተመድና የትግራይ ግጭት

የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት አብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባል ሐገራት ተወካዮች ከቃላት ልዩነት በስተቀር ጉዳዩ ወደ አፍሪቃ ሕብረት እንዲመለስ ተናግረዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:48

የፀጥታዉ ምክር ቤት ስብሰባና የኢትዮጵያ አቋም

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከእንግዲሕ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ምክር ቤት መነጋገሪያ ርዕሥ እንደማይሆን የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ። በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሠበብ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር ስለገጠመችዉ ዉዝግብ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት ባደረገዉ ዉይይት አስተያየት የሰጡት የምክር ቤቱ አባላት ሶስቱ ሐገራት ልዩነታቸዉን ለማስወገድ በአፍሪቃ ሕብረት ሸምጋይነት እንዲደራደሩ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት አብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባል ሐገራት ተወካዮች ከቃላት ልዩነት በስተቀር ጉዳዩ ወደ አፍሪቃ ሕብረት እንዲመለስ ተናግረዋል። አምባሳደር ዲና ትግራይ ዉስጥ ያለዉን ወታደራዊ ቀዉስ በተመለከተ በሰጡት መግለጫም «የሕወሓት አማፂ ቡድን ሰበረዉ» ያሉትን የተከዜ ድልድይን ለመጠገን መንግስታቸዉ እየጣረ መሆኑን አስታዉቀዋል።ሳዑዲ አረቢያ ከሐገሯ እንዲወጡ ከወሰነችባቸዉ ኢትዮጵያን መካከል ከ21 ሺሕ የሚበልጡ ሐገራቸዉ መግባታቸዉን ገልፀዋልም።

ሠለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች