የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 04.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መግለጫ

የአውሮፕላኑ አብራሪዎች አደጋዉን ለማስወገድ ማድረግ የነበረባቸዉን ቅድመ ጥንቃቄ በሙሉ አድርገዋል። አብራሪዎቹ አደጋውን ለመከላከል፣ በአሜሪካዉ የበረራ ደሕንነት ባለስልጣን የፀደቀዉን፣ የአዉሮፕላኑ አምራች ኩባንያ የቦይንግ የአስቸኳይ ወይም የአደጋ ጊዜ መመሪያን በሙሉ ገቢራዊ ቢያደርጉም አዉሮፕላኑን ባፍንጫዉ ቁልቁል ከመስመጥ ሊያስቆሙት አልቻሉም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10

ፓይለቶች አደጋዉን ለማስወገድ ማድረግ የነበረባቸዉን ቅድመ ጥንቃቄ በሙሉ አድርገዋል

ባለፈዉ መጋቢት 1 ቢሾፍቱ አጠገብ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 302፣ ቦይንግ 737 MAX 8 አውሮፕላን አብራሪዎች አዉሮፕላኑን ከአደጋ ለማዳን የቦይንግ መመሪያ የሚያዘዉን ሁሉ ጥረት ማድረጋቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥለአደጋዉ የተደረገዉን ምርመራ የመጀመሪያ ዘገባ ዛሬ ይፋ ሲያደርግ እንዳስታወቀዉ የአውሮፕላኑ አብራሪዎች (ፓይለቶች) አደጋዉን ለማስወገድ ማድረግ የነበረባቸዉን ቅድመ ጥንቃቄ በሙሉ አድርገዋል። አብራሪዎቹ አደጋውን ለመከላከል፣ በአሜሪካዉ የበረራ ደሕንነት ባለስልጣን (FAA) የፀደቀዉን፣ የአዉሮፕላኑ አምራች ኩባንያ የቦይንግ የአስቸኳይ ወይም የአደጋ ጊዜ መመሪያን በሙሉ ገቢራዊ ቢያደርጉም አዉሮፕላኑን ባፍንጫዉ ቁልቁል ከመስመጥ ሊያስቆሙት አልቻሉም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፌስ ቡክ ገፁ እንደዘገበዉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም በአብራሪዎቻችን እንኮራለን፣ በአብራሪዎች ማስልጠኛ ተቋማችንም እንኮራለን ብለዋል።በመጋቢት አንዱ አደጋ አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ የነበሩ 157 ሰዎች በሙሉ አልቀዋል።  የአደጋውን የተመለከው ሙሉ ምርመራ አንድ ዓመት እንደሚወስድ ተገልጿል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቶአል። ሚኒስትርዋ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስና የምርመራ ቡድኑ መሪ አቶ አምድዬ አያሌዉ በጋራ በመሆን ለጋዜጠኞች ማብራርያ ሰጥተዋል ቦታዉ ላይ የነበረዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉ ልኮልናል። ።


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic