የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሠር | ኢትዮጵያ | DW | 31.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሠር

የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ሞጋ ፊሪሳ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ከታሰሩት የድርጅታቸዉ ባለሥልጣን አንዱ የተያዙት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለሕ በሚል እንደሆነ የመንግሥት መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል

default


የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) የተሰኘዉ የሐገሪቱ መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ሁለት ባለሥልጣናቱና ሌሎች ሰባት አባላቱ በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች መታሠራቸዉን አስታወቀ።የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ሞጋ ፊሪሳ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ከታሰሩት የድርጅታቸዉ ባለሥልጣን አንዱ የተያዙት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለሕ በሚል እንደሆነ የመንግሥት መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል።ሁለተኛዉ ባለሥልጣን ሥለታሰረቡት ምክንያት ግን መገናኛ ዘዴዎቹ የዘገቡት ነገር።ዶክተር ሞጋ እንዳሉት የተቀሩት ሰባቱ የድርጅቱ አባላት የተያዙት ደቡብ ኢትዮጱያ ዉስጥ ነዉ።ዶክተር ሞጋን ስቱዱዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸዉ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic