የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ወቀሳ፦ መንግስትና ኤርትራ | ኢትዮጵያ | DW | 27.01.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ወቀሳ፦ መንግስትና ኤርትራ

«ሻቢያ-መራሽ» ባሉት የኤርትራ መንግሥት፣ በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሽብር ድርጊት

default

ዶክተር ነጋሶ

ከሰሞኑ በአፋር-ደንከል በረሃ፣ 5 አውሮፓውያን አገር ጎብኝዎች ስለተገደሉበትና ተጨማሪ 2 ጎብኝዎችና ቁጥራቸው ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን ተጠልፈው የተወሰዱበት ሁኔታ እጅግ በጣም እንዳሳዘነው፤ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፣ መድረክ ፤ አስታወቀ። የመድረክ አመራር አባላት፤ ከዚህ ጋር በማያያዝ፤ በየጊዜው «ሻቢያ-መራሽ» ባሉት የኤርትራ መንግሥት፣ በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሽብር ድርጊት ፤ መንግሥት ከህዝብ እየደበቀ ያለበት ሁኔታ ፤ በአጠቃላይ የሀገሪቱን የደሽንነት ሁኔታ ሥጋት ላይ የጣለ ነው በማለትም መንግሥትን አጥብቆ መውቀሱን ፤ ታደሰ እንግዳው የላከልን ዘገባ ያስረዳል የኤርትራ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል።ኤርትራ ዉንጀላዉን አጣጥላ ነቅፋዋለች። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር አቶ ዓሊ አብዶ ወቀሳ-ወግዝቱን ዛሬ «የሻገተ ቲያትር» ብለዉታል።

ታደሰ እግዳዉ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic