የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ዉይይት | ኢትዮጵያ | DW | 10.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ዉይይት

የዶክተር ጫኔ ኢዴፓ ከሌሎች አምስት ሐገር አቀፍ አቻዎቹ ጋር በመሆን የመደራደሪያ የጋራ ረቂቅ ሐሳብ አቅርቧል።ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የየራሳቸዉን ሐሳብ ማቅረባቸዉ ተዘግቧል።በገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ በኩል ሥለተደረገዉ ዝግጅት ለማወቅ የፓርቲዉን ሹማምንት በሥልክ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንሞክርም፤ ያዉ እንደተለመደዉ፤ ሥልካቸዉን አያነሱም

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10

የተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ዉይይት

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ)ና ሐገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች ሁለተኛ ዙር ድርድር ለማድረግ መዘጋጀታቸዉን አስታወቁ።የሐገሪቱን ፖለቲካዊ ዉዝግቦችና ችግሮች ለማቃለል ይረዳል በተባለዉ ድርድር ላይ የ22 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ይካፈላሉ።በመጪዉ ሳምንት ሮብ ይጀመራል ለተባለዉ ድርድር ገዢዉ ፓርቲም፤ ተቃዋሚዎቹም የመደራደሪያ ረቂቅ ሐሳቦችን ማዘጋጀታቸዉን በየፊናቸዉ አስታዉቀዋል። 

አንዳንዶች ዉይይት ይሉታል።ሌሎች ድርድር።ደግሞ ሌሎች ሁለቱንም።አንዱም ተባለ ሁለቱ በርግጥ እንግዳ አይደለም።የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ ሐገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን እንደምትከተል ካስታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ፖለቲከኞችዋ አምስትም፤ አስርም ዓመት እያሰለሱ ሲነጋገሩ ደግሞ በተቃራኒዉ ወዲያዉ ሲፋረሱ እነሆ 26ኛ ዓመታቸዉ።
 ብዛት ወይም ቁጥራቸዉን-እየቀነሱ-እየደመሩ፤ ርዕስ፤ ተወካዮቻቸዉን እንደየወቅቱ ሁኔታ እየለዋወጡ የሚነጋገሩ፤ደሞ በተቃራኒዉ የሚወነጃጀሉት ፖለቲከኞች ዘንድሮም «ድርድ» ማለት የጀመሩት ሐገሪቱ በሕዝባዊ ተቃዉሞ ስትናወጥ ነዉ።በዚሕም ሰበብ አንዳድ ታዛቢዎች ድርድሩን የገዢዉን ፓርቲ ከጭንቅ ለመገላገል የተቀመረ፤ ዘመነ-ሥልጣኑን ለማራዘም ያለመ፤ በዉጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎችን ያገለለ በማለት ይነቅፉታል።በድርድሩ የሚሳተፈዉ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)ም ይሕን አላጣዉም።
ይሁንና የፓርቲዉ ፕሬዝደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ እንደሚሉት ድርድሩ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች አስፈላጊ፤ ጠቃሚም ነዉ።
                         

የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አብረሐ ደስታ በበኩላቸዉ ድርድር ገዢዉን ፓርቲ ከመታገያ ሥልቶች አንዱ ነዉ ባይናቸዉ።አቶ አብረሐ እንደሚሉት፤ በድርድሩ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) የሚወከለዉ አረና በሌሎች መስኮች የሚያነሳቸዉን ጥያቄዎች በድርድሩም  ያነሳል።
                                    
 ዶክተር ጫኔም ተመሳሳይ አቋም ነዉ ያላቸዉ።
                                      
ካሰቡት ለመድረስ የዶክተር ጫኔ ኢዴፓ ከሌሎች አምስት ሐገር አቀፍ አቻዎቹ ጋር በመሆን የመደራደሪያ የጋራ ረቂቅ ሐሳብ አቅርቧል።ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የየራሳቸዉን ሐሳብ ማቅረባቸዉ ተዘግቧል።በገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ በኩል ሥለተደረገዉ ዝግጅት ለማወቅ የፓርቲዉን ሹማምንት በሥልክ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንሞክርም፤ ያዉ እንደተለመደዉ፤ ሥልካቸዉን አያነሱም።ለፓርቲዉ ቅርበት ያላቸዉ መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት ግን ኢሕአዴግም በድርድሩ መነሳት አለባቸዉ ያላቸዉን ሐሳቦች አርቅቋል።

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic