የኢትዮጵያ ብርቅ ድንቅ የዱር እንስሳትና ዐራዊት | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 21.11.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የኢትዮጵያ ብርቅ ድንቅ የዱር እንስሳትና ዐራዊት

በዓለም ውስጥ ከሚገኙት ብርቅዬ ዐራዊት መካከል ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍኛ ቦታዎች ፣ እንደ ድመት አይጥ እያደኑ በመመገብ የሚኖሩት ፣ የኢትዮጵያ ተኩላዎች ወይም ቀይ ቀበሮዎች የተሰኙት ናቸው። በየዕለቱ ከአንድ መቶ የማያንሱ የእንስሳትና ዐራዊት

default

ዓይነቶች ከፕላኔታችን ገጸ- ምድር ይጠፋሉ።

መንበረ እንስሳትና ዐራዊት፤ በተለያዩ ምክንያቶች፤ በሰው ሠራሽ ጭምር ማለት ነው፤ ችግር ሲደቀንባቸው የከተሞች መንበረ ዐራዊት ፣ ዘር ለመጠበቅ አብነት ይኖራቸው ይሆን? ከመጨነቅ የተነሣ አንዳንድ ለእንስሳት ጥበቃ የቆሙ ጠበብት የሚሠነዝሩት ጥያቄ ነው። በተደራጁ የከተማ መንበረ እንስሳትና ዐራዊት በጠባብ ቦታ፣ የተለያዩ የዱር እንስሳትና ዐራዊት ፤ አእዋፍም እንዲኖሩ ቢገደዱም የተፈጥሮ ባህርያቸው ፣ ያን ያህል ለውጥ እንደማይታይበት ይነገራል ፤ ይሁን እንጂ፤ በጫካም ሆነ በዋሻ፤ በወንዝ ፣ በቀላይ ወይም በሸለቆና ሣር ምድር (ሳቫና) መኖር የለመዱ እንስሳትና ዐራዊት የትኛውን ሊመርጡ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም።

BdT Deutschland Zoo Frankfurt Affenbaby

በጤና አጠባበቅ፤ አመጋገብ፤ የከተሜዎቹ ክብካቤ ሲደረግላቸው፣ በዱር በገደል የሚኖሩት ይበልጥ የሚያረካቸው፣ ነጋ- ጠባ የሰው ዐይን ሳያዩ በበረሃ በነጻነት መኖሩ ሳይሆን አይቀርም። እርግጥ ፤ በዱር በገደል የሚኖሩት እንስሳት ሰውን እንደሚጠናወቱ ተውሳኮች፣ እነርሱንም የሚያሠጉ በሽታዎች አልፎ-አልፎ ያጠቋቸዋል። በሽታን የመቋቋም ጥንካሬ ያላቸው የመኖራቸውን ያህል አንዳንዶች ፤ በተለይም በዓለም ውስጥ ብርቅ ድንቅ የሚሰኙት ዐራዊትም ሆኑ እንስሳት በታቸለው ሁሉ ጥረት ካልተደረገ የሚጠፉበት አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ነው የሚነገረው።

ከአነዚህም ውስጥ፤ ብርቅ ድንቅ ከሚሰኙት የኢትዮጵያ ዐራዊትና እንስሳት መካከል ቀይ ቀበሮዎች ፣ ወይም የኢትዮጵያ ተኩላዎች በመባል የታወቁት ይገኙበታል።

Scientific American መጽሔት በዚህ ወር መግቢያ ገደማ ኢትዮጵያ ውስጥ 500 ቀይ ቀበሮዎች እንደቀሩና ቀሪዎቹም በሽታን በመቋቋም ረገድ ተፈጥሮአቸው ደካማ በመሆኑ እንዳይጠፉ ያሠጋል በማለት Extinction Coundown በሚል ርእስ ጽፏል። ይህ አሳሳቢ አባባል እስከምን እውን ነው?

በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር፤የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ መሪ (ዳይሬክተር ) አቶ እውነቱ ብላታን ደበላ ማብራሪያ የተካተተበትን ጥንቅር ያድምጡ።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 21.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16nkT
 • ቀን 21.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16nkT