የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ርምጃና የባሉሙያ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 01.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ርምጃና የባሉሙያ አስተያየት

ብሔራዊ ባንክ ግሽበቱን ለመቀነስ ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች የባንኮች የመጠባበቂያ ተቀማጭ ምጣኔን በእጥፍ ማሳደግ እና ከብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔን ማሻሻል ይገኝበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

«መፍትሄው ግብርናውን መደጎም ነው»

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ይረዳል ያለውን በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ ስርጭት የሚቀንስ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊሲን ከዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ። ብሔራዊ ባንኩ ግሽበቱን ለመቀነስ ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች የባንኮች የመጠባበቂያ ተቀማጭ ምጣኔን በእጥፍ ማሳደግ እና ከብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔን ማሻሻል ይገኝበታል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የኢኮኖሚ ባለሙያ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር ከሁሉም ቀዳሚ ግብርናን መደጎም ነው ይላሉ።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች