የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቻን ውድድር ተሰናበተ | ስፖርት | DW | 12.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቻን ውድድር ተሰናበተ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በአፍሪቃ ሀገራት ሻምፒዮና (CHAN) ላይ ለመሳተፍ ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ ባካሄደው ጨዋታ ያለ ጎል በመለያያቱ ወደ ውድድሩ ሳያልፍ ቀረ፡፡ ሩዋንዳ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በድምር ውጤት 3 ለ 2 በመርታት ሞሮኮ በምታስተናግደው ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድሉን አግኝታለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በአፍሪቃ ሀገራት ሻምፒዮና (CHAN) ላይ ለመሳተፍ ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ ባካሄደው ጨዋታ ያለ ጎል በመለያያቱ ወደ ውድድሩ ሳያልፍ ቀረ፡፡ ሩዋንዳ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በድምር ውጤት 3 ለ 2 በመርታት ሞሮኮ በምታስተናግደው ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድሉን አግኝታለች፡፡ ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በአፍሪቃ አህጉር የሚጫወቱ ተጫዎቾች ብቻ በሚሳተፉበት በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በየዞናቸው ባደረጉት ጨዋታ በተጋጣሚዎቻቸው ተሸንፈው ከውድድር ውጭ ሆነው ነበር፡፡ ኬንያን ተክታ በውድድሩ እንድትሳተፍ ተጠይቃ የነበረችው ግብጽ የጨዋታ መርሃ ግብር መጋጨትን ምክንያት በማድረግ ራሷን አግላለች፡፡ የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በግብጽ ፈንታ ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በደርሶ መልስ ተጫውተው አሸናፊው ወደ ውድድሩ እንዲቀላቀል ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት የመጀመሪያ ጨዋታውን በአዲስ አበባ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ አቻው 3 ለ 2 ተረትቷል፡፡ የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን ዛሬ በኪጋሊ አማቩቢ በመባል ከሚጠራው የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉት ዋልያዎቹ ግብ ማስቆጠር ተስኗቸው ከውድድር ውጭ ሆነዋል፡፡ 

ተስፋለም ወልደየስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ