የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 13.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ

የውስጥ ችግሮቻቸውን ጉባኤ ጠርተው እንዲፈቱ ማሳሰቢያ ለሰጣቸው ለመኢአድና ለአንድነት ፓርቲዎች የተባሉትን እንዲያደርጉ ተጨማሪ ጊዜ እንደተሰጣቸው አስታውቋል ።

Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከቀትር በኋላ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነትንና ሰማያዊ ፓርቲን የሚመለከት መግለጫ ሰጥቷል ። ቦርዱ በዚሁ መግለጫው የውስጥ ችግሮቻቸውን ጉባኤ ጠርተው እንዲፈቱ ማሳሰቢያ ለሰጣቸው ለመኢአድና ለአንድነት ፓርቲዎች የተባሉትን እንዲያደርጉ ተጨማሪ ጊዜ እንደተሰጣቸው አስታውቋል ። በዚሁ መግለጫ ይቅርታ የመጠየቂያ የጊዜ ገደብ ያስቀመጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠውም ገልጿል ። ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ዝርዝሩን በስልክ ጠይቄው ነበር ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic